የአለም አቀፉ የፖስታ ህብረት 28ኛው ጠቅላላ ጉባዬ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ባሳየው የላቀ አፈፃፀም የ2024 የፈጣን መልእክት የደንበኞች አገልግሎት ጥራት ሽልማትን ተቀብሏል።
ሽልማቱ የተሰጠው የአለም አቀፉ የፖስታ ሕብረት ባስቀመጣቸው የአገልግሎት ጥራት መመዘኛ መሰረት ሲሆን ከተወዳዳሪ ሀገራት መካከል ብልጫ በማግኘቱም መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ሽልማት ተቋማችን እያስመዘገበ ላለው ሁለንተናዊ ለውጥ ትልቅ አቅም የሚሰጥ በመሆኑ ለመላው የኢትዮጵያ ፖስታ ቤተሰብ በተመዘገበው ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን! 🏆 🏆 🏆