የኢትዮዽያ ፖስታ ከፍተኛ የስራ ሐላፊዎች ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የበላይ አመራሮች ጋር በቀጣይ በጋራ መስራት በሚቻለባቸው ጉዳዮች ላይ በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
ውይይቱም በዋነኝነት የፓስፖርት ስርጭት አገልግሎቱን በመላው ኢትዮዽያ በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ሲሆን በቅርቡ በመላው ሀገሪቱ ውስጥ ባሉ የኢትዮጵያ ፖስታ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች አገልግሎቱ የሚጀመር ይሆናል።





