Ethiopost welcomes Secretary General of PAPU

የፓን አፍሪካ ፖስታ ህብረት (PAPU) ዋና ፀሐፊ ለሆኑት ለክቡር ዶ/ር ሲፉንዶ ቺፍ ሞዮ ደማቅ አቀባበል ስናደርግላቸው በታላቅ ክብር ነው። በጉብኝታቸውም ወቅት የኢትዮጵያፖስታን እድገት በሚመለከት ገንቢ ውይይት አድርገን ለወደፊቱ የትብብር መንገዶችን ቃኝተናል። ጉብኝቱ የኢትዮጵያፖስታን አገልግሎቶችን አጠቃላይ ጉብኝት ያቀፈ ሲሆን ይህም ክቡር ዶ/ር ሲፉንዶ ቺፍ ሞዮ ስለአሰራራችን የሰፋ ግንዛቤ እንዲኖራቸው አስችሏል። በተጨማሪም፣ ለፖስታ አገልግሎት ሰራተኞች ክፍት የሆነውን የልጆች ማቆያ አብረው ጎብኝተዋል።

ይህ ስብሰባ በ የኢትዮጵያፖስታ እና በፓን አፍሪካ ፖስታ ህብረት (PAPU) መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና ሀሳብ ለመለዋወጥ ጠቃሚ እድል ሰጥቷል።

Ethiopost is honored to extend a warm welcome to His Excellency Dr. Sifundo Chief Moyo, the Secretary General of the Pan African Postal Union (PAPU). During his visit, we had a constructive discussion on the trajectory of Ethiopost and explored potential avenues for collaboration in the future.

The visit encompassed a comprehensive tour of Ethiopost’s services, allowing H.E. Dr. Sifundo Chief Moyo to gain firsthand insights into our operations. Additionally, we had the privilege of showcasing the Ethiopost daycare facility, highlighting our commitment to the holistic well-being of our community.

We look forward to the prospect of future collaborations that will contribute to the advancement of postal services on both a national and continental scale.

More updates Ethiopost

News

በኢትዮጵያ ፖስታ እና በእልባት ማኔጅመንት እና ቴክኖሎጂ ሶሉሽን መካከል በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውል ተፈረመ፡፡

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ፖስታን በመወከል ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር እና  በእልባት ማኔጅመንት እና ቴክኖሎጂ ሶሉሽን በኩል ደግሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ነፃነት ራያ  ተፈራርመዋል፡፡

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ከኢት-ስዊች አክሲዮን ማሕበር ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

በስምምነት ፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ እና ኢትስዊች አክሲዮን ማሕበር የተፈራረሙት ስምምነት የኤጀንት ኔትወርክ ማኔጅመንት መተግበሪያን በጋራ ለማበልፀግ ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ነባር የቦርድ አባላት የሽኝት እና ለአዲሱ ቦርድ አባላት የአቀባበል ስነስርአት ተካሄደ።

በሽኝት ሥነሥርዓቱ ላይ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ የተቋሙ የስትራቴጂ እቅድ ግቡን እንዲመታ የቦርድ አባላቱ ያበረከቱትን ጉልህ አስተዋፅኦ በማንሳት በኢትዮጵያ ፖስታ ውስጥ ትልቁን ታሪክ እንደፃፉ እና ትልቅ ምስጋና እና ክብር እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

Read More »