በኢትዮጵያ ፖስታ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ እና በኢግልድ የኢንዱስትሪ ዉጤቶች ግዥ እና ሽያጭ ዘርፍ ም/ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባዬ ገዛኸኝ የተፈረመው ይህ አጋርነት የኢግልድ የኢንዱስትሪ ዉጤቶችን በኢትዮጵያ ፖስታ ቅርንጫፍ ፖስታ ቤቶች በኩል ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና በኦንላይን የኢግልድን የኢንዱስትሪ ዉጤቶች ለሚገበያዩ ደንበኞች በሚመርጡት ቦታ ዕቃዎችን ለማድረስ የሚያስችል ነው::
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፖስታ ተደራሽነቱን ከማስፋት አንፃር የኢግልድን ቅርንጫፍ ቢሮዎች ለሚሰጣቸዉ የተለያዩ አገልግሎቶች በፍራንቻይዝነት መጠቀምን ያካትታል ::
News
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮጵያ ፖስታን ጎበኙ።
በክቡር አቶ እውነቱ አለነ የተመራ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት እና የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ፖስታ ሁለንተናዊ ተሃድሶ እንዲሁም አጠቃላይ የስራ ክንውን ላይ ውይይት እና የመስክ ጉብኝት አካሂደዋል።