የኢትዮጵያ ፖስታ 131ኛ ዓመት የምስረታ በዓል።

የኢትዮጵያ ፖስታ ላለፉት 131 ዓመታት በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም ግንባር ቀደም የግንኙነት ምሰሶ በመሆን ሰዎችን ከሰዎች ተቋማትን ከተቋማት በማገናኘት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ባህላዊ ትስስር እንዲጠነክርና የንግድ ልውውጥ እንዲያድግ የበኩሉን አስተዋፅዖ ሲያበረክት የቆየ አንጋፋ የህዝብ ተቋም ነው።

በቀድሞ ጊዜ ከነበረው የፖስታ ልውውጥ አሰራር አንስቶ እስከ አሁኑ ዘመናዊ የሎጂስቲክስና የዲጂታል ዘመን ከሁኔታዎችና ወቅታዊ ፍላጐቶች ጋር እራሱን በማስተዋወቅና በማዘመን እንዲሁም የአገልግሎት አድማሱንና ተደራሽነቱን በማስፋት ላለፉት አንድ መቶ ሠላሣ አንድ ዓመታት በትጋትና በአገልጋይነት መንፈስ ተጉዟል።

ዛሬም ይህን ትውልዶች የተቀባበሉትን አስደናቂ ምዕራፍ 131ኛ የምስረታ በዓል ስናከብር የዚህ ጉዞ አካል የሆኑትን ውድ ሰራተኞቻችንን፣ ውድ ደንበኞቻችንን እና አጋሮቻችንን በማመስገንና ላበረከቱት አስተዋፅዖ እውቅና በመስጠት ነው።

በቀጣይም አኩሪ የሕዝብ አገልጋይነት ታሪካችንን ሰንቀን ያሁኑንና ቀጣዩን ትውልድ ለማገልገል ይረዳን ዘንድ ቴክኖሎጂን በማቀፍ፣ አዳዲስ የአሰራር ስልቶችን በመንደፍና የደንበኞችን ፍላጎት ማዕከል በማድረግ ሁሌም ከትናንቱ በተሻለ ልናገለግልዎ ዝግጁ መሆናችንን በመግለጽ ነው።

መልካም 131ኛ ዓመት!

More updates Ethiopost

News

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ላለፉት ተከታታይ አመታት በተሰሩት የሪፎርም ስራዎች ላይ ተመስርቶ ‹‹በጥልቀት እና በስፋት›› በሚል ስትራቴጂክ ፕላን ተቋሙን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራ ያለው ስራ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ሙዚየም 50ኛ ዓመት የወርቅ እዩ ቤልዩ ክብረ በዓል!

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ በክብረ በዓሉ ላይ ለተገኙት እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን እንደተቋም የፖስታ ሙዚየሙ ላይ እየተሠሩ ያሉ የማስፋፊያ ሥራዎች እንዳሉ እና በቅርቡ ይፋ እንደሚደረጉ ገልጸዋል፡፡

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ የሥራ አመራሮች የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም እቅዶች ላይ ከሰራተኞች ጋር ውይይት አደረጉ።

በውይይቱ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ የአቅርቦት እና ፋሲሊቲ ቺፍ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ጋሻው መርሻ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል፤ አያይዘውም በ2017 በጀት ዓመት ለነበረው አፈጻጸም ሁሉም የኢትዮጵያ ፖስታ ሰራተኛ ምስጋና ሊቸረው እንደሚገባ አንስተው በቀጣይም ይኸው የሥራ መነሳሳት እና ተልዕኮዎቻችንን በድል የመወጣት ባሕል ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

Read More »