የዓለምአቀፍ የፖስታ ህብረት በፖሰታ አባል አገራት መካከል ለሚደረግ የፖስታ መልዕክቶች ልውውጥ /UPU Remuneration System/ የክፍያ ስርዓት በተመለከተ ለስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ሥልጠና ሰጠ፡፡
የዓለምአቀፍ ፖስታ ህብረት የክፍያ ስርዓት ኤክስፐርት በሆኑት በሚስተር ፊሊፕ ግሮንዴይን ለአራት ተከታታይ ቀናት ከግንቦት 4- ግንቦት 7/2017 ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን በስልጠናው ከተለያዩ ክፍሎች የተውጣጡ ሰላሳ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በአጠቃላይ ስልጠናው የዓለምአቀፍ ፖስታ ህብረት የክፍያ ስርዓት ቴክኒካዊ አሰራር እውቀት ለማሰጨበጥ ያለመ በመሆኑ ከስልጠናው በተገኘው እውቀት መሰረት አሰራራችንን በማሻሻል ረገድ ትልቅ አስተዋፅዖ እንደሚኖሮው ታምኖበታል።














