የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፉ የፖስታ ሕብረት የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) ጥራት ምዘና ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነ።

🎉🎉🎉እንኳን ደስ አለን!🎉🎉🎉

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፉ የፖስታ ሕብረት የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) ጥራት ምዘና ከአፍሪካ ቀዳሚ በመሆን ከመላው ዓለም ደግሞ 6ኛ ደረጃ ላይ መመደቡ በይፋ ተገልጿል።

ይህ ክብር የኢትዮጵያ ፖስታ በዘመናዊ የፖስታ አገልግሎት፣ በፈጣን ሎጂስቲክስ አቅርቦት እና በደንበኛ ተኮር የአገልግሎት ጥራት ላይ ያደረገውን ተከታታይ ማሻሻያ የሚያሳይ ሲሆን፣ ድርጅቱ በአፍሪካ እና በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ የፖስታ አገልግሎት ተቋም እየሆነ መምጣቱን ያረጋግጣል።

ይህ ውጤት የኢትዮጵያ ፖስታ ሠራተኞች ትጋት፣ የአመራሮች ቁርጠኝነት ድምር ውጤት በመሆኑ ለሁሉም የተቋሙ ማሕበረሰብ ታላቅ ምስጋና ይገባል፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ወደፊትም ዘመናዊ፣ አስተማማኝ እና ደንበኛ ተኮር አገልግሎት በማቅረብ በሀገራችን የሎጂስቲክስና የፖስታ ዘርፍ ልማት ውስጥ ያለውን ሚና በቀጣይነት ያጠናክራል።

More updates Ethiopost

News

በኢትዮጵያ ፖስታ እና በአሐዱ ባንክ መካከል በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

የኢትዮጵያ ፖስታ በአገልግሎት ማስፋፋት እና በፋይናንስ ዘርፍ የሚደረጉ ትብብሮችን በማጠናከር ለህብረተሰቡ የቀረበ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለማቅረብ እየሠራ ባለው ሥራ ላይ ይህ የስምምነት ፊርማ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ከM-PESA ኢትዮጵያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ።

የኢትዮጵያ ፖስታ ከ M-PESA ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ባሉት ከ 1000 በላይ ቅርንጫፎች አማካይነት የM-PESA አገልግሎትን እንደ ዋና ወኪል በመሆን ለደንበኞቹ ማቅረብ የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ 132ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እና የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበረ፡፡

በዕለቱ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ለመላው የኢትዮጵያ ፖስታ ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ ፖስታ 132ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እንዲሁም ለዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጉብኝት አካሄዱ፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ጉብኝቱ ላይ ባዩዋቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች እና የሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እየተሰሩ ባሉት ሥራዎች ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ የአየር ኃይላችንን 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ያዘጋጃቸውን አራት አይነት ታሪካዊ ቴምብሮች በይፋ አስመርቋል።

ዛሬ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የተመሰረተበትን 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አክብሯል። የኢትዮጵያ ፖስታ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ ለመዘከር ያሳተማቸውን አራት አይነት ልዩ የመታሰቢያ ቴምብሮች በይፋ አስመርቋል።

Read More »