የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጉብኝት አካሄዱ፡፡

ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎቹ ወደ ኢኒስቲቲዩቱ ሲደርሱ የኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘውዴ ለሥራ ኃላፊዎቹ የተቋሙን የስራ እቅድ እንዲሁም በተቋሙ ውስጥ ስለሚገኙ አዳዲስና ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አገልግሎቶች በተመለከተ ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ጉብኝቱ ላይ ባዩዋቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች እና የሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እየተሰሩ ባሉት ሥራዎች ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በተያያዘም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተቋሙ ሀገርን የሚያኮራ እና የሚያስመሰግን ሥራ እየሠራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ ለኢትዮጵያ ፖስታ ይጠቅማሉ የተባሉ የቴክኖሎጂ መገልገያዎች ለከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎቹ የቀረቡ ሲሆን ለኢትዮጵያ ፖስታ የወደፊት ስትራቴጂ እቅድ ደጋፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡

ጉብኝቱ በቀጣይ ሁለቱ ተቋማት በጋራ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መሰረት የሚጥል እንደሆነም በጉብኝቱ ላይ ተገልጿል፡፡

More updates Ethiopost

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን የሙዚየም ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተበረከተለት።

የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ “የተከፋፈለችውን ዓለም የሚያስተሳስሩ ሙዚየሞች” በሚል እጅግ ወቅታዊ መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ በረከት ዘውዴ እና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Read More »
News

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ የመታሰቢያ ቴምብሮች በይፉ አስመረቀች።

የኢትዮጵያ ፖስታ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና ታሪካዊ እሴቶቻችንን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። ይህንን ታላቅ ኩነት አስመልክቶ የወጣው ልዩ የመታሰቢያ ቴምብርም ተቋማችን የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ስኬት ለዓለም በማብሰር ረገድ ያለውን ሚና የሚያጎላ ነው።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ስምምነት ተፈራረሙ።

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ኩባንያ “ልባም” የተሰኘውን የዲጂታል የህይወት መድን መተግበሪያ በመላው ሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ መድረክ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ተሸላሚ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU) የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ቀዳሚነቱን ሲያረጋግጥ፣ ከመላው ዓለም ደግሞ 6ኛ ደረጃን በመያዝ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል።

Read More »