የኢትዮጵያ ፖስታ 132ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እና የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበረ፡፡

በዕለቱ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ለመላው የኢትዮጵያ ፖስታ ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ ፖስታ 132ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እንዲሁም ለዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም የዘንድሮውን የ132ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ልዩ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ፖስታ በ2025 ከአፍሪካ በ ኢ.ኤም.ኤስ የአገልግሎት ጥራት አሸናፊ እንዲሁም ከዓለም 6ኛ ደረጃ መያዙ በታወቀበት ወቅት መከበሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም ድርጅቱ በዘመናዊ አገልግሎት፣ በደንበኛ ተኮር አስተዳደር እና በአገልግሎት ጥራትም ጭምር እየተሻሻለ መምጣቱን ያሳያል ብለዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የ132ኛ ዓመቱን በማስመልከት የተለያዩ ዲፓርትመንቶች ዋና የሥራ ኃላፊዎች በለፉት 3 ዓመታት በኢትዮጵያ ፖስታ ውስጥ የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶችን በተመለከተ ለዝግጅቱ ተሳታፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪም በዕለቱ የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ፖስታ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር ወ/ሮ ትእግስት በቀለ የተመራ የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን በውይይቱም ላይ የሴቶች ውስጣዊ ጥንካሬ፣ አይበገሬ ማንነት እና የ“እችላለሁ” መንፈስ በተግባር ተገልጿል፡፡

More updates Ethiopost

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን የሙዚየም ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተበረከተለት።

የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ “የተከፋፈለችውን ዓለም የሚያስተሳስሩ ሙዚየሞች” በሚል እጅግ ወቅታዊ መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ በረከት ዘውዴ እና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Read More »
News

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ የመታሰቢያ ቴምብሮች በይፉ አስመረቀች።

የኢትዮጵያ ፖስታ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና ታሪካዊ እሴቶቻችንን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። ይህንን ታላቅ ኩነት አስመልክቶ የወጣው ልዩ የመታሰቢያ ቴምብርም ተቋማችን የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ስኬት ለዓለም በማብሰር ረገድ ያለውን ሚና የሚያጎላ ነው።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ስምምነት ተፈራረሙ።

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ኩባንያ “ልባም” የተሰኘውን የዲጂታል የህይወት መድን መተግበሪያ በመላው ሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ መድረክ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ተሸላሚ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU) የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ቀዳሚነቱን ሲያረጋግጥ፣ ከመላው ዓለም ደግሞ 6ኛ ደረጃን በመያዝ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል።

Read More »