በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የኘላንና ልማት ሚኒስቴር ቢሮ ያወጣውን ሪፖርት መሰረት በማድረግ ለሰራተኞች አጠቃላይ በተለያዪ ዘርፎች የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ገለጻ አድርገዋል። ይህንንም ተከትሎ በቀረበውም ሪፖርት ላይ በታየውን አበራታች ውጤት ሰራተኞች መልካም አስተያየቶችን ሰተውበታል። በቀጣይም የተገኙ ውጤቶችን በማስቀጠል፣ በተቀመጡ የትኩረት አቅጣጫዎች እና መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ልዪ ትኩረት በማድረግና በጋራ በመረባረብ ለበለጠ ውጤት ለመትጋት በመስማማት ውይይቱ ተጠናቋል።

News
የኢትዮጵያ ፖስታ በደንበኞች አገልግሎት ጥራት ተሸላሚ ሆነ።
የአለም አቀፉ የፖስታ ህብረት 28ኛው ጠቅላላ ጉባዬ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ባሳየው የላቀ አፈፃፀም የ2024 የፈጣን መልእክት የደንበኞች አገልግሎት ጥራት ሽልማትን ተቀብሏል።













