የኢትዮጵያ ፖስታ ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ። የመግባቢያ ስምምነቱ በኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ እና የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃሚድ ኪኒሶ መካከል ተፈርሟል። ይህ ስምምነት 700 በላይ በሚሆኑ የኢትዮጵያ ፖስታ ቅርንጫፎች የሰነዶችን ምዝገባ አገልግሎትን እንዲያካሄድ የሚስችላቸው ሲሆን ይህም በተደራሽነት ፣ ወጥነት ያለው የክፍያ አሰራርን ከመዘርጋት አኳያ እና ሙያዊ ስነምግባርን የተላበሰ አገልግሎት ከመስጠት አንጳር ትልቅ እምርታ ያመጣል ተብሎ ይታመናል። ይህም አገልግሎት በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በተመረጡ የኢትዮጵያ ፖስታ ቅርንጫፎች ውስጥ መሰጠት ይጀምራል።
የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን የሙዚየም ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተበረከተለት።
የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ “የተከፋፈለችውን ዓለም የሚያስተሳስሩ ሙዚየሞች” በሚል እጅግ ወቅታዊ መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ በረከት ዘውዴ እና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡












