የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ መድረክ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ተሸላሚ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU) የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ቀዳሚነቱን ሲያረጋግጥ፣ ከመላው ዓለም ደግሞ 6ኛ ደረጃን በመያዝ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል።

የተመዘገቡ ድሎች፡-

🥇 የ2025 የEMS አጠቃላይ አገልግሎት ጥራት ሽልማት (EMS Performance Award):- በአህጉራችን 1ኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ 6ኛ የተቀመጠ ብቃት ማረጋገጫ!

🥈የ2025 የEMS የደንበኞች አገልግሎት ሽልማት (EMS Customer Care Award):- በአህጉራችን 1ኛ ደረጃ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በ3ኛ ነት የተቀመጠ ስኬት!

ይህም ለደንበኞቻችን የምንሰጠው አገልግሎት የዓለም አቀፍ መለኪያ መስፈርቶችን በሚገባ ሟሟላቱን፣ ለሰው ተኮር አገልግሎት የሰጠነውን ትኩረት የመሰከረ እና ከዓመት ዓመት በከፍተኛ መሻሻል ለተከታታይ ሶስት ዓመታት የተጎናጸፍነው ሽልማት ነው።

እነዚህ ዓለም አቀፍ እውቅናዎች የኢትዮጵያ ፖስታ ሁለንተናዊ ተቋማዊ ሪፎርም ውጤታማነት ማሳያ ከመሆኑም በላይ፣ በዓለም አቀፍ የፈጣን መልእክት እና የሎጂስቲክስ መድረክ ላይ የሀገራችንን ተወዳዳሪነት የሚያረጋግጥ ነው።

ለሁላችሁም የኢትዮጵያ ፖስታ ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ! ከጎናችን ስለሆናችሁ ከልብ እናመሠግናለን።

ይህ ድል ለቀጣይ የተሻለ አገልግሎት የገባነውን ቃል ኪዳን ማደሻችን ነው!

More updates Ethiopost

News

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ መድረክ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ተሸላሚ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU) የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ቀዳሚነቱን ሲያረጋግጥ፣ ከመላው ዓለም ደግሞ 6ኛ ደረጃን በመያዝ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል።

Read More »
News

በኢትዮጵያ ፖስታ እና በአሐዱ ባንክ መካከል በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

የኢትዮጵያ ፖስታ በአገልግሎት ማስፋፋት እና በፋይናንስ ዘርፍ የሚደረጉ ትብብሮችን በማጠናከር ለህብረተሰቡ የቀረበ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለማቅረብ እየሠራ ባለው ሥራ ላይ ይህ የስምምነት ፊርማ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ከM-PESA ኢትዮጵያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ።

የኢትዮጵያ ፖስታ ከ M-PESA ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ባሉት ከ 1000 በላይ ቅርንጫፎች አማካይነት የM-PESA አገልግሎትን እንደ ዋና ወኪል በመሆን ለደንበኞቹ ማቅረብ የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ 132ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እና የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበረ፡፡

በዕለቱ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ለመላው የኢትዮጵያ ፖስታ ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ ፖስታ 132ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እንዲሁም ለዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

Read More »