የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ስምምነት ተፈራረሙ።

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ኩባንያ “ልባም” የተሰኘውን የዲጂታል የህይወት መድን መተግበሪያ በመላው ሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የኢትዮጵያ ፖስታ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽመልስ ገድለ ጊዮርጊስ የፈረሙት ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የኢትዮጰያ ፖስታን ሰፊ ተደራሽነት በመጠቀም ህብረተሰቡ የዲጂታል የህይወት መድን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል ነው።

ወ/ሮ ትዕግስት የህይወት መድን ለዜጎች ያለውን ዘላቂ ዋስትና ጠቅሰው ተቋሙ የኢትዮጵያ ፖስታን ተደራሽነት ለመጠቀም መወሰኑ የሚደነቅ መሆኑን ሲገልጹ፣ አቶ ሽመልስ በበኩላቸው ከአንጋፋው ተቋም ጋር መስራት ለኢንሹራንስ ዘርፉ ዕድገት ትልቅ መሰረት እንደሚጥል አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ፖስታ ከባንኮችና ከቴሌኮም ኩባንያዎች ጋር በዲጂታል ፋይናንስ ሲሰራ የቆየ ቢሆንም፣ የዲጂታል የህይወት መድን አገልግሎት መስጠት የሚጀምርበት ይህ ስምምነት ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

More updates Ethiopost

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን የሙዚየም ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተበረከተለት።

የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ “የተከፋፈለችውን ዓለም የሚያስተሳስሩ ሙዚየሞች” በሚል እጅግ ወቅታዊ መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ በረከት ዘውዴ እና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Read More »
News

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ የመታሰቢያ ቴምብሮች በይፉ አስመረቀች።

የኢትዮጵያ ፖስታ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና ታሪካዊ እሴቶቻችንን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። ይህንን ታላቅ ኩነት አስመልክቶ የወጣው ልዩ የመታሰቢያ ቴምብርም ተቋማችን የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ስኬት ለዓለም በማብሰር ረገድ ያለውን ሚና የሚያጎላ ነው።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ስምምነት ተፈራረሙ።

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ኩባንያ “ልባም” የተሰኘውን የዲጂታል የህይወት መድን መተግበሪያ በመላው ሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ መድረክ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ተሸላሚ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU) የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ቀዳሚነቱን ሲያረጋግጥ፣ ከመላው ዓለም ደግሞ 6ኛ ደረጃን በመያዝ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል።

Read More »