የኢትዮጵያ ፖስታ ከ1.4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ ለመቄዶኒያ አበረከተ።

የኢትዮጵያ ፖስታ ማህበራዊ ኃላፊነቱን የመወጣት አንድ አካል አድርጎ በተለያዩ ዙሮች ለመቄዶኒያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ዛሬም ይህን መልካም ተግባሩን በማስቀጠል፣ ግምታቸው 1,424,500.00 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሃያ አራት ሺህ አምስት መቶ) ብር የሆኑ ልዩ ልዩ ድጋፎችን ለመቄዶኒያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል አስረክቧል።

ለተቋሙ የተደረገው ይህ ሰብአዊ ድጋፍ ልዩ ልዩ አልባሳትን፣ የሃይማኖት መጻሕፍትን እና ሌሎች ለተረጂዎች አስፈላጊ የሆኑ ቁሶችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ የሰው ሀብት አስተዳደር ቺፍ ኦፊሰር አቶ ተሾመ ቢረዳ እንደገለጹት፤ ተቋሙ ማህበራዊ ግዴታውን ለመወጣት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል። አቶ ተሾመ አክለውም፣ ድርጅቱ ከገንዘብ እርዳታ ባለፈ በቁሳቁስ ጭምር የሚያደርገው ድጋፍ በቀጣይነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በመጨረሻም በዕለቱ የድጋፍ ርክክቡ በሚከናወንበት ወቅት በማዕከሉ በሚረዱ አባቶችና እናቶች የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።

More updates Ethiopost

News

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ስምምነት ተፈራረሙ።

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ኩባንያ “ልባም” የተሰኘውን የዲጂታል የህይወት መድን መተግበሪያ በመላው ሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ መድረክ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ተሸላሚ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU) የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ቀዳሚነቱን ሲያረጋግጥ፣ ከመላው ዓለም ደግሞ 6ኛ ደረጃን በመያዝ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል።

Read More »
News

በኢትዮጵያ ፖስታ እና በአሐዱ ባንክ መካከል በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

የኢትዮጵያ ፖስታ በአገልግሎት ማስፋፋት እና በፋይናንስ ዘርፍ የሚደረጉ ትብብሮችን በማጠናከር ለህብረተሰቡ የቀረበ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለማቅረብ እየሠራ ባለው ሥራ ላይ ይህ የስምምነት ፊርማ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ከM-PESA ኢትዮጵያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ።

የኢትዮጵያ ፖስታ ከ M-PESA ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ባሉት ከ 1000 በላይ ቅርንጫፎች አማካይነት የM-PESA አገልግሎትን እንደ ዋና ወኪል በመሆን ለደንበኞቹ ማቅረብ የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።

Read More »