የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የ2018 በጀት ዓመት የ 9 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቦ አስገመገመ።
በግምገማው ላይ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ መለሰ መናን ጨምሮ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ ኮሬ እንዲሁም የቋሚ ኮሚቴው አባላት ተገኝተዋል፡፡
በእለቱ ሪፖርቱን ያቀረቡት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ እና የኢትዮጵያ ፖስታ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ፤ ተቋማችን ባለፉት አስር ወራት ውስጥ በአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፣ የውስጥ ገቢን በማሳደግ፣ የፖስታ አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ በማዘመን እንዲሁም የመልካም አስተዳደር እሴቶችን በማስፈን ረገድ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ስኬቶችና አበረታች ተግባራት እንዲሁም ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በዝርዝር አብራርተዋል።
የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ መለሰ መና በበኩላቸው፤ ይህ የግምገማ መድረክ ድርጅቱ እስካሁን ያከናወናቸውን ጠንካራ ተግባራት ይበልጥ እንዲያጠናክር እና በቀጣይም የላቀ አገራዊ ውጤት እንዲያስመዘግብ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ከቋሚ ኮሚቴው አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች አማካኝነት ዝርዝር ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን፤ ተቋማችን የተሰጡትን ገንቢ አስተያየቶች በመውሰድ የጀመራቸውን የማሻሻያና የሪፎርም ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።












