ለኢትዮጵያ ፖስታ የዋናው መሥሪያ ቤት እና የዲስትሪክት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የ”PROPEL” ስትራቴጂ እና የአሠራር ሂደት መግለጫዎች (SOPs) ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
የስልጠናው ዋና ዓላማ አዲሱን የ”PROPEL” ስትራቴጂ እና የተቋሙን የአሠራር ሂደት መግለጫዎች (SOPs) ወደ ተግባር በማሸጋገር፣ የኢትዮጵያ ፖስታ የሚያከናውናቸው ተግባራት ያላቸውን ተቋማዊ አፈጻጸም እና ሀገራዊ ፋይዳ ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ላይ ጠንካራ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር ነው።
በስልጠናው መክፈቻ መርሐግብር ላይ የዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወካይ እና የተቋሙ ቺፍ ኮመርሻል ኦፊሰር የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ወደ ትግበራ በገባው ብሔራዊ ገዢ ስትራቴጂ፣ እንዲሁም በተቋሙ አዲስ የ”PROPEL” ስትራቴጂ ትግበራ እና ሀገራዊ ፋይዳው ዙሪያ ያተኮረ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ማብራሪያ ለተሳታፊዎች ሰጥተዋል።
ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ 8 ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ፣ በሁሉም የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቅራቢነት፣ በየሥራ ክፍሉ የአሠራር ሂደት መግለጫዎች (SOPs) ላይ ሰፋ ያሉ ማብራሪያዎች ቀርበው ጥልቅ ውይይቶች ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ስልጠናው ተቋሙ ለቀጣይ ዓመታት ያስቀመጠውን ራዕይ እና ግብ በተቀናጀ ስትራቴጂ እና ወጥ በሆነ የአሰራር ሂደት ለማሳካት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ታምኖበታል።














