የኢትዮጵያ ፖስታ የ 2016 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም እና የ2017 ዓ.ም እቅድ ላይ ሠራተኞቹ ጋር ውይይት አድርጓል።

ባሳለፍነው ሳምንት የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የስራ አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ ስራ ክፍል ሃላፊዎች የ2016 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ 2017 ዓ.ም ዕቅድን በተመለከተ በተለያዪ የሃገሪቱ ክፍሎች ካሉ ቅርንጫፍ ፖስታ ቤት ሠራተኞች ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም በ2016 ዓ.ም የታዩ ጠንካራ ጎኖች ተበረታተው እንዲቀጥሉ ያወሳው ውይይቱ በአንጻሩ በበጀት አመቱ የነበሩ ክፍተቶችን በመለየት የእርምት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል።

More updates Ethiopost

News

የኢትዮጵያ ፖስታ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲቱት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

ይህ አጋርነት ዘመናዊ የካርታ አሰራርን በኢትዮጵያ ፖስታ ሎጅስቲክስ ማዕቀፍ ውስጥ በማካተት የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን እና ጥራትን ለማሳደግ ያለመ ነው:: ይህንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ፈጣን እና አስተማማኝ የቤት ለቤት እደላ አገልግሎትን በማሳለጥ የደንበኞችን እርካታን ማሻሻል ይቻላል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር የመገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የሰው ሃብት አስተዳደር ሃላፊ የሆኑት አቶ ተሾመ ቢረዳ እንዲሁም የንብረት አስተዳደር ክፍል ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ይፍቱስራ መኮንን መገልገያ ቁሳቁሶቹን ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር ያስረከቡ ሲሆን የመቄዶኒያ አረጋዉያን የቡራኬ ስነስርዓት አድርገዋል።

Read More »
News

የ2024 የእስያ ፊላቴሊክ ኤግዚቢሽን በቻይና።

በሻንጋይ የተካሄደው የ2024 የኤዥያ አለም አቀፍ የቴምብር ኤግዚቢሽን የእስያን ባህል በፊላቴሊ ጥበብ የሚያሳይ ደማቅ በዓል ነበር። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች አስደናቂውን የቴምብር ማሳያ አድንቀዋል፣ እያንዳንዱም የቴምብር ስራዎች ታሪክን፣ ጥበብን እና ወግን ይናገራሉ።

Read More »
News

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮጵያ ፖስታን ጎበኙ።

በክቡር አቶ እውነቱ አለነ የተመራ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት እና የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ፖስታ ሁለንተናዊ ተሃድሶ እንዲሁም አጠቃላይ የስራ ክንውን ላይ ውይይት እና የመስክ ጉብኝት አካሂደዋል።

Read More »