የኢትዮጵያ ፖስታ በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ማህበረሰቦች ድጋፍ አደረገ፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን በደረሰ የመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ማህበረሰቦች የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር አስተባባሪነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም በመገኘት በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ የመሬት ናዳ ለተጎዱ ወገኖች ማቋቋሚያ የሚሆን የ1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በሰው ሃብት ሥራ አመራር ዲፓርትመንት ቺፍ ኢፊሰር በሆኑት አቶ ተሾመ ቢረዳ አስረክበናል፡፡ በአደጋው ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ተጎጂ ቤተሰቦች እና የአካባቢው ማህበረሰብ መፅናናትን እንመኛለን።

More updates Ethiopost

News

የ2017 ዓ.ም አጠቃላይ አገር አቀፍ የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ገለጻ ለኢትዮጵያ ፖስታ ሰራተኞች ተደረገ።

የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የኘላንና ልማት ሚኒስቴር ቢሮ ያወጣውን ሪፖርት መሰረት በማድረግ ለሰራተኞች አጠቃላይ በተለያዪ ዘርፎች የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ገለጻ አድርገዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከፍተኛ የስራ አመራሮች የኢትዮጵያ ፖስታን ጎበኙ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከፍተኛ የስራ አመራሮች በዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ እና በምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ኃ/ሚካኤል የተመራ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ልዑክ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና መስሪያ ቤትን የጎበኙ ሲሆን በድርጅቱ የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ላይ ስትራቴጂካዊ ውይይት አድርገዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ 131ኛ ዓመት የምስረታ በዓል።

በቀድሞ ጊዜ ከነበረው የፖስታ ልውውጥ አሰራር አንስቶ እስከ አሁኑ ዘመናዊ የሎጂስቲክስና የዲጂታል ዘመን ከሁኔታዎችና ወቅታዊ ፍላጐቶች ጋር እራሱን በማስተዋወቅና በማዘመን እንዲሁም የአገልግሎት አድማሱንና ተደራሽነቱን በማስፋት ላለፉት አንድ መቶ ሠላሣ አንድ ዓመታት በትጋትና በአገልጋይነት መንፈስ ተጉዟል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲቱት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

ይህ አጋርነት ዘመናዊ የካርታ አሰራርን በኢትዮጵያ ፖስታ ሎጅስቲክስ ማዕቀፍ ውስጥ በማካተት የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን እና ጥራትን ለማሳደግ ያለመ ነው:: ይህንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ፈጣን እና አስተማማኝ የቤት ለቤት እደላ አገልግሎትን በማሳለጥ የደንበኞችን እርካታን ማሻሻል ይቻላል።

Read More »