የኢትዮጵያ ፖስታ የ9 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቀረበ።

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የ2018 በጀት ዓመት የ 9 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቦ አስገመገመ።

በግምገማው ላይ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ መለሰ መናን ጨምሮ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ ኮሬ እንዲሁም የቋሚ ኮሚቴው አባላት ተገኝተዋል፡፡

በእለቱ ሪፖርቱን ያቀረቡት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ እና የኢትዮጵያ ፖስታ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር  ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ፤ ተቋማችን ባለፉት አስር ወራት ውስጥ በአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፣ የውስጥ ገቢን በማሳደግ፣ የፖስታ አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ በማዘመን እንዲሁም የመልካም አስተዳደር እሴቶችን በማስፈን ረገድ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ስኬቶችና አበረታች ተግባራት እንዲሁም ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በዝርዝር አብራርተዋል።

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ መለሰ መና በበኩላቸው፤ ይህ የግምገማ መድረክ ድርጅቱ እስካሁን ያከናወናቸውን ጠንካራ ተግባራት ይበልጥ እንዲያጠናክር እና በቀጣይም የላቀ አገራዊ ውጤት እንዲያስመዘግብ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

በመጨረሻም ከቋሚ ኮሚቴው አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች አማካኝነት ዝርዝር ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን፤ ተቋማችን የተሰጡትን ገንቢ አስተያየቶች በመውሰድ የጀመራቸውን የማሻሻያና የሪፎርም ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

More updates Ethiopost

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን የሙዚየም ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተበረከተለት።

የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ “የተከፋፈለችውን ዓለም የሚያስተሳስሩ ሙዚየሞች” በሚል እጅግ ወቅታዊ መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ በረከት ዘውዴ እና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Read More »
News

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ የመታሰቢያ ቴምብሮች በይፉ አስመረቀች።

የኢትዮጵያ ፖስታ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና ታሪካዊ እሴቶቻችንን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። ይህንን ታላቅ ኩነት አስመልክቶ የወጣው ልዩ የመታሰቢያ ቴምብርም ተቋማችን የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ስኬት ለዓለም በማብሰር ረገድ ያለውን ሚና የሚያጎላ ነው።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ስምምነት ተፈራረሙ።

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ኩባንያ “ልባም” የተሰኘውን የዲጂታል የህይወት መድን መተግበሪያ በመላው ሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ መድረክ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ተሸላሚ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU) የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ቀዳሚነቱን ሲያረጋግጥ፣ ከመላው ዓለም ደግሞ 6ኛ ደረጃን በመያዝ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል።

Read More »