በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሃገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ዲጂታል የገበያ እድል ለመፍጠር የተዘጋጀው ፕሮጀክት፥ በዛሬው እለት ለየኢትዮጵያ ፖስታ የኢ-ኮሜርስ ዲጂታል የገበያ ማእከልን ለማቅረብ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት እና ሲ.ኤስ.ኤም ከአፍሪኮም ጋር በጋራ በመሆን በዛሬው እለት ተፈራርመዋል። የኢትዮጵያ ፖስታ ይህን የኢ-ኮሜርስ ዲጂታል የገበያ ማእከልን በመምራት ብሎም የሎጂስቲክስ ክፍተቱን በመሙላት እንከን የለሽ እና ቀልጣፋ የአገልግሎት አቅርቦትን ለማረጋግጥ የሚሰራ ይሆናል።
ይህ ፕሮጀክት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን በመደገፍ የኢ-ኮሜርስ መልክዓ ምድሩን ለመለወጥ በማለም የላቀ እርምጃ ወደፊት ያራምዳል። ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ጠንካራ የገበያ ቦታ በመፍጠር ለዳበረ ዲጂታል ኢኮኖሚ መንገድም ይከፍታል።
Follow us on our social media platforms | Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest | TikTok |