Ethiopost receives the 2023 Postal Excellence Award in Riyadh as the lead for the Africa Region! Our Deputy CEO, Gashaw Mersha, had the honor of receiving the award on our behalf.
This recognition is the result of Ethiopost’s exemplary performance across key metrics evaluating designated postal operators. These past few years, Ethiopost has been hard at work implementing institutional reforms that address service quality, delivery, speed, and accessibility, among many others. We are proud that this effort has culminated in this recognition as a regional leader in postal excellence by the Universal Postal Union’s Extraordinary Congress held in Riyadh, Saudi Arabia.
የኢትዮጵያፖስታ በሪያድ የአፍሪካ ሪጅን የPostal Excellence Award ተሸላሚ ሆነ!
የዓለም ፖስታ ሕብረት በየዓመቱ በሚያደርገው የፖስታ አገልግሎት ሰጪዎች ምዘና የኢትዮጵያ ፖስታ በ2023 ዓ.ም. የአፍሪካ ሪጅን አሽናፊ መሆኑ ተገለጸ። ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጋሻው መርሻ ሽልማቱን ተቀብለዋል።
የኢትዮጵያ ፖስታ ባለፉት ዓመታት ተቋማዊ ሪፎርሞችን በመተግበር የአገልግሎት አሠጣጥ ማሻሻያዎች፣ የመልዕክት ፍጥነትና ተደራሽነት ላይ በርካታ ለውጦች እንዳመጣ ይታወቃል። ይህንንም ተከትሎ የዓለም ፖስታ ሕብረት በሚያደርገው የአግልግሎት ጥራት ምዘና ከዓመት ዓመት አፈጻጸሙን ሲያሻሽል ቆይቶ ዛሬ በሪያድ፣ ሳውዲ አረቢያ በተደረገው የሕብረቱ ልዩ ኮንግረስ ላይ የአፍሪካ ሪጅንን በመምራት የፖስታ ልሕቀት ሽልማት ተቀብሏል።