የኢትዮጵያ ፖስታ የሰራተኞች ህብረት ቀን ላይ ከዋና መስሪያ ቤት እንዲሁም ከሁሉም የዲስትሪክት ቅርንጫፍ የተወጣጡ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች ከጥር 24 እስከ ጥር 25፣ 2017 ዓ.ም ሱሉልታ በሚገኘው በያያ ቪሌጅ በድምቀት አክብሯል። በዝግጅቱ በሁለቱም ጾታ የእግር ኳስ ግጥሚያ፣ የገመድ ጉተታ፣ የጆንያ ዝላይ እና ሌሎች ጨዋታዎች የተካሄደ ሲሆን ለአሸናፊዎች የዋንጫ እና የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በዚሁ ዝግጅት ላይ ከሁሉም የዲፓርትመንት ክፍሎች የዓመቱ ኮከብ ሰራተኛ የእውቅና እና የሽልማት ስነ-ስርዓትም ተካሂዷል። በተጨማሪም ድርጅቱን ለረጅም አመታት ያለመታከት ላገለገሉ ሰራተኞች የሽኝት ስነ-ስርዓት ከሽልማት ጋር ተበርክቶላቸዋል።