ለአራት ኪሎ ቅርንጫፍ ደንበኞቻችን በሙሉ
የፖስታ አገልግሎት ተደራሽነት እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ እንረዳለን። የአራት ኪሎ ቅርንጫፋችን (ጆሊ ባር) በቅርብ ጊዜ እየተካሄዱ ባሉ የመሰረተ ልማት ስራዎች ምክንያት አገልግሎት መስጠት ቢያቆምም በቅርንጫፉ በኩል ይመጡ የነበሩ መልዕክቶችዎ እንዲሁም የፖስታ ሳጥን አገልግሎት ውልዎ ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን ልናረጋግጥልዎ እንወዳለን። በአራት ኪሎ ቅርንጫፍ ይሰጥ የነበረውን የፖስታ ሳጥን አገልግሎት በአራዳ ቅርንጫፋችን ማግኘት ይችላሉ።
ስለ ትብብርዎ እናመሰግናለን።
ቱሪስት ሆቴል አቅራቢያ በሚገኘው ቅርንጫፋችን:- https://maps.app.goo.gl/vPxheEtna8gXAUf8A