News and Updates from Ethiopost
የኢትዮጵያ ፖስታ – የሰራተኞች ህብረት ቀን በድምቀት ተከበረ።
የኢትዮጵያ ፖስታ የሰራተኞች ህብረት ቀን ላይ ከዋና መስሪያ ቤት እንዲሁም ከሁሉም የዲስትሪክት ቅርንጫፍ የተወጣጡ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች ከጥር 24 እስከ ጥር 25፣ 2017 ዓ.ም ሱሉልታ በሚገኘው በያያ ቪሌጅ በድምቀት አክብሯል።

የኢትዮጵያ ፖስታ በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ማህበረሰቦች ድጋፍ አደረገ፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን በደረሰ የመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ማህበረሰቦች የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ በ2016 ዓ.ም እየተከናወነ በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል!
የኢትዮጵያ ፖስታ በ2016 ዓ.ም “የምትተክል አገር፣የሚያፀና ትውልድ!” በሚል መሪ ሀሣብ እየተከናወነ በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል!

የኢትዮጵያ ፖስታ የታዳጊዎችን የደብዳቤ ፅሁፍ ውድድር በደማቅ ሁኔታ አጠናቋል።
አለም አቀፍ የሙዚየም ቀን አከባበርን በማስቀጠል የኢትዮጵያ ፖስታ የታዳጊዎችን የደብዳቤ ፅሁፍ ውድድር የመዝጊያ ዝግጅት በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል። በውድድሩ ተሳትፈው ከአንድ እስከ ሶስት ለወጡ ታዳጊዎች የኢትዮጵያፖስታ የታብሌት ሽልማት አበርክቷል።

የኢትዮጵያ ፖስታ የበላይ አመራሮች እና ሰራተኞች ስትራይድ ኤክስፖን ጎበኙ።
ይህ ጉብኝት የንግድ ግንኙነታችንን ለማሻሻል እና አዳዲስ የቴክኖሎጂ እድገቶችን በተመለከተ ጠቃሚ ግንዛቤዎችን ለማግኘት እድል ሰጥቷል።

አለም አቀፍ የሙዚየም ቀን በኢትዮጵያ ፖስታ
አለምአቀፍ ሙዚየም ሣምንትን ከእኛ ጋር ያክብሩ! የ130 አመታት ታሪክን በዋናው ፖስታ ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው በፖስታ እና ፊላቴሊ ሙዚየም ይጎብኙ።

የኢትዮጵያ ፖስታ የኢ-ኮሜርስ ዲጂታል የገበያ ማዕከልን ለማቅረብ ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት እና ከሲኤስኤም አፍሪኮም ጋር በጋራ ተፈራርሟል።
በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሃገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ዲጂታል የገበያ እድል ለመፍጠር የተዘጋጀው ፕሮጀክት፥ በዛሬው እለት ለየኢትዮጵያ ፖስታ የኢ-ኮሜርስ ዲጂታል የገበያ ማእከልን ለማቅረብ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት እና ሲ.ኤስ.ኤም ከአፍሪኮም ጋር በጋራ በመሆን ተፈራርመዋል።