በትናንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከፍተኛ የስራ አመራሮች በዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ እና በምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ኃ/ሚካኤል የተመራ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ልዑክ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና መስሪያ ቤትን የጎበኙ ሲሆን በድርጅቱ የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ላይ ስትራቴጂካዊ ውይይት አድርገዋል። የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ባደረጉት የስድስት ወር የስራ አፈጻጸም ገለፃ ላይ ቁልፍ ስኬቶችን፣ ተግዳሮቶችን እና የወደፊት የእድገት እቅዶችን ያቀረቡ ሲሆን ገለጻውን ተከትሎ አገልግሎቶችን ማዘመን፣ ማስፋፋት እና ፈጠራን ማሳደግ ላይ ያተኮረ ውይይት ተደርጓል። በቀጣይም የትኩረት እና ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በኩል ተሰጥቷል።

News
የኢትዮጵያ ፖስታ በደንበኞች አገልግሎት ጥራት ተሸላሚ ሆነ።
የአለም አቀፉ የፖስታ ህብረት 28ኛው ጠቅላላ ጉባዬ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ባሳየው የላቀ አፈፃፀም የ2024 የፈጣን መልእክት የደንበኞች አገልግሎት ጥራት ሽልማትን ተቀብሏል።













