በዛሬው ዕለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ተወካዮች በኢትዮጵያ ፖስታ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ጉብኝት እና ውይይት አደረጉ። ውይይቱ በዋነኝነት የኢትዮጵያ ፖስታ አሁን ያለበትን ደረጃ ካለው ሰራተኛ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ሃላፊዎች ድረስ ያለውን እይታ የቃኘ ነበር። በተጨማሪም ከጉብኝቱ እንደተገነዘቡት የኢትዮጵያ ፖስታ በሁሉም መስክ በሚባል ደረጃ አመርቂ ለውጥ እያስመዘገበ መሆኑን ጠቅሰው ከሰራተኛው በኩል ለተነሱ ጥያቄዎች ከሃላፊዎች ማብራርያ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቅቋል።
የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን የሙዚየም ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተበረከተለት።
የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ “የተከፋፈለችውን ዓለም የሚያስተሳስሩ ሙዚየሞች” በሚል እጅግ ወቅታዊ መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ በረከት ዘውዴ እና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡













