የኢትዮጵያ ፖስታ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።
የስምምነቱ ዋና አላማ የመንገድ ፈንድ እድሳትን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የአገልግሎት መስጫ ቅርንጫፎች እና በዓመታዊ የተሽከርካሪ ቴክኒክ ደህንነት ምርመራ ተቋማት እንዲኖር ማድረግ ሲሆን ሁሉንም አገልግሎት በአንድ ቦታ መስጠት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል። በመሆኑም የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ቁጥጥር ባለስልጣን የኢትዮጵያ ፖስታ ሕጋዊ ውክል ባለው የመንገድ ፈንድ ሰርተፍኬት እድሳት ስራ ላይ በባለስልጣኑ አገልግሎት መስጫ ቅርንጫፎች በመገኘት ተጨማሪ ደንበኞች አገልግሎቱን ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡
ይህ ስምምነት አገልግሎት አሰጣጡንና የመረጃ አያያዝ ስርዓትን በማዘመን የደንበኞችን የአገልግሎት እርካታ እንደሚጨምር የታመነ ሲሆን ጥናትና የአሰራር ማሻሻያ በማካሄድ ዉጤታማ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ብቃት የማረጋገጥ ተልዕኮ ያለው እንደሆነም በስብሰባው ላይ ተገልጿል፡፡











