የኢትዮጵያ ፖስታ የሥራ አመራሮች የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም እቅዶች ላይ ከሰራተኞች ጋር ውይይት አደረጉ።

በውይይቱ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ የአቅርቦት እና ፋሲሊቲ ቺፍ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ጋሻው መርሻ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል፤ አያይዘውም በ2017 በጀት ዓመት ለነበረው አፈጻጸም ሁሉም የኢትዮጵያ ፖስታ ሰራተኛ ምስጋና ሊቸረው እንደሚገባ አንስተው በቀጣይም ይኸው የሥራ መነሳሳት እና ተልዕኮዎቻችንን በድል የመወጣት ባሕል ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በውይይቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ በአምስቱ ዋና ዋና የስትራቴጂክ ምሰሶዎችን መሰረት ባደረጉ አፈጻጸሞች እና ቀጣይ እቅዶች ላይ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በሰው ሀብት አስተዳደር ዙርያ የሚኖሩ የተለያዩ የአሰራር ማሻሻያዎችም እንዲሁ ሰፊ ገለጻ ተደርጎባቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ በሁለተኛው ምዕራፍ ላይ ከሰራተኞች ለተነሱት አጠቃላይ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሾችን የሰጡ ሲሆን በውይይቱ መጠናቀቂያም ድርጅቱ እያስመዘገበ ላለው ዘርፈ ብዙ ስኬት ዋና ባለቤት ሰራተኛው መሆኑን ገልጸው፤ ሁሉን አቀፍ እድገት ለማስመዝገብ እየተሰራ እንደሆነ እና የቀጣይ በጀት ዓመት ግቦችን በጋራ ለማሳካት የሁሉም ሰራተኞች አስተዋጾ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

More updates Ethiopost

News

በኢትዮጵያ ፖስታ እና በእልባት ማኔጅመንት እና ቴክኖሎጂ ሶሉሽን መካከል በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውል ተፈረመ፡፡

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ፖስታን በመወከል ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር እና  በእልባት ማኔጅመንት እና ቴክኖሎጂ ሶሉሽን በኩል ደግሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ነፃነት ራያ  ተፈራርመዋል፡፡

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ከኢት-ስዊች አክሲዮን ማሕበር ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

በስምምነት ፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ እና ኢትስዊች አክሲዮን ማሕበር የተፈራረሙት ስምምነት የኤጀንት ኔትወርክ ማኔጅመንት መተግበሪያን በጋራ ለማበልፀግ ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ነባር የቦርድ አባላት የሽኝት እና ለአዲሱ ቦርድ አባላት የአቀባበል ስነስርአት ተካሄደ።

በሽኝት ሥነሥርዓቱ ላይ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ የተቋሙ የስትራቴጂ እቅድ ግቡን እንዲመታ የቦርድ አባላቱ ያበረከቱትን ጉልህ አስተዋፅኦ በማንሳት በኢትዮጵያ ፖስታ ውስጥ ትልቁን ታሪክ እንደፃፉ እና ትልቅ ምስጋና እና ክብር እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

Read More »