የኢትዮጵያ ፖስታ ሰራተኞች ‹‹በመትከል ማንሰራራት›› በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለውን ሰባተኛውን ዙር ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር አካሄዱ።
በዛሬው እለት በተካሄደው በዚሁ መርሐ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሞጆ ከተማ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው የችግኝ መትከያ ስፍራ በመገኘት የራሳቸውን አሻራ በማሳረፍ እና የመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎችን በማበረታታት ከ2000 በላይ ችግኞች እንዲተከሉ አድርገዋል።
በተጨማሪም በችግኝ ተከላው ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ፖስታ ሰራተኞች እንደ ሀገር የተጀመረው ሀገርን አረንጓዴ የማልበስ ንቅናቄ እንዲሳካ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ በማበርከታቸውና የዚህ በጎ ተግባር ተሳታፊ በመሆናቸው እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።













