የኢትዮጵያ ፖስታ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል የሰራቸውን የቴምብር ሥራዎች በይፋ አስመርቋል።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን የመታሰቢያ ቴምብሮቹንም የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በጋራ በመሆን ይፋ አድርገዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አንጋፋው የኢትዮጵያ ፖስታ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ታሪኮች በተለያዩ ጊዜያት በቴምብር ሥራዎች እየቀረጸ ሲያስቀምጥ የኖረ ተቋም እንደሆነ ገልጸው ዩኒቨርሲቲያቸውም ከኢትዮጵያ ፖስታ ጋር በመስራቱ ኩራት እና ደስታ እንደሚሰማው ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም የተቋማትን የዘመናት አበርክቶት ለአለም በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ያለው እና የሚገኘው የኢትዮጵያ ፖስታ ሌሎች ዝግጅታቸው የተጠናቀቁ የተቋማት ቴምብሮችን ከተቋማቱ ጋር በመሆን በየጊዜው ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚያደርግ እና አሁንም ይህንኑ አገልግሎት ለሚሹ ተቋማት በሩ ክፍት እንደሆነ በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡












