በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አስተባባሪነት መቀመጫውን ሩሲያ ላይ ያደረገው የኢ-ኮሜርስ ኩባንያ ‘’RWB’’ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ፖስታ ተገኝተው ከከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
የ RWB ልኡካን ቡድን የኢትዮጵያ ፖስታ ሲደርስ በኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ እና በከፍተኛ አመራር ቡድኑ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
በውይይቱ ላይም አለም ዓቀፍ የኢ-ኮሜርስ ንግዱ ላይ ሁለቱ አጋር ድርጅቶች በጋራ ሊሰሩባቸው ስለሚችሉ ነጥቦች በማንሳት ጥልቅ ውይይት አድርገዋል፡፡
ከውይይቱም ባሻገር የልኡካን ቡድኑ አባላት በኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራአስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ እና በከፍተኛ አመራር ቡድኑ አማካኝነት የተለያዩ የኢትዮጵያ ፖስታን ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች የሥራ ሁኔታ እንዲሁም የኢ-ኮሜርስ መጋዘኖችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱም ወቅት ጎብኚዎቹ በኢትዮጵያ ፖስታ ውስጥ የተመለከቱት የአሠራረር ሁኔታ ከጠበቁት በላይ እንደሆነ እና ደስ እንደተሰኙበት ተናግረው በቀጣይ በጋራ ሊሠሩባቸው የሚችሉባቸውን መንገዶች ማመቻቸት እና ወደሥራው መግባት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡












