የኢትዮጵያ ፖስታ የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዕቅድ ውይይቱ አጠናቀቀ፡፡

በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ የድርጅቱ አመራሮች በተሳተፉበት እና ለተከታታይ አራት ቀናት ሲካሄድ በቆየው መድረክ ላይ እንደተገለጸው፤ ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት 3.85 ቢሊዮን ብር ገቢ ሰብስቧል። ይህ አፈጻጸም ከባለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ30 በመቶ ዕድገት ያሳየ ሲሆን፣ ተቋሙ በሌሎች ቁልፍ የአፈጻጸም መለኪያዎችም አመርቂ ውጤት ያስመዘገበበት ስኬታማ ዓመት ሆኖ አልፏል።

በተጨማሪም የቀደመውን “በጥልቀት እና በስፋት” የተሰኘውን የስትራቴጂ እቅድ በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቀ ሲሆን፣ አዲስ የሶስት ዓመታት ስትራቴጂ በመቅረፅ ቴክኖሎጂ-መር እና ደንበኛ-ተኮር አገልግሎቶችን ለማቅረብ ከምንጊዜውም በላይ በላቀ መነሳሳት ወደ ተግባር ለመለወጥ ጠንካራ አቋም ተይዟል።

በመዝጊያ ስነ-ስርዓቱ ላይ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡት የጂ.ፒ.ኦ (GPO)፣ የአዲስ አበባ እና ምስራቅ ዲስትሪክቶች የዋንጫ እና የእውቅና ሰርተፊኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ በመዝጊያ ንግግራቸው፥ አዲሱን የስትራቴጂክ ፕላን ወደ ሙሉ ተግባር ለመቀየር እና የ2019 በጀት ዓመት እቅዶችን ስኬታማ ለማድረግ የጠንካራ አመራር እና የሰራተኞች የተቀናጀ ርብርብ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። ዋና ሥራ አስፈፃሚው አክለውም እያንዳንዱ አመራርና ሰራተኛ የተጣለበትን ሀላፊነት በመወጣት ተቋሙ የጀመረውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ዳር ለማድረስ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርበዋል።

More updates Ethiopost

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን የሙዚየም ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተበረከተለት።

የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ “የተከፋፈለችውን ዓለም የሚያስተሳስሩ ሙዚየሞች” በሚል እጅግ ወቅታዊ መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ በረከት ዘውዴ እና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Read More »
News

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ የመታሰቢያ ቴምብሮች በይፉ አስመረቀች።

የኢትዮጵያ ፖስታ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና ታሪካዊ እሴቶቻችንን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። ይህንን ታላቅ ኩነት አስመልክቶ የወጣው ልዩ የመታሰቢያ ቴምብርም ተቋማችን የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ስኬት ለዓለም በማብሰር ረገድ ያለውን ሚና የሚያጎላ ነው።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ስምምነት ተፈራረሙ።

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ኩባንያ “ልባም” የተሰኘውን የዲጂታል የህይወት መድን መተግበሪያ በመላው ሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ መድረክ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ተሸላሚ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU) የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ቀዳሚነቱን ሲያረጋግጥ፣ ከመላው ዓለም ደግሞ 6ኛ ደረጃን በመያዝ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል።

Read More »