Ethiopost Receives EMS Customer Care Award 2023.

የኢትዮጵያፖስታ ለ2023 የኢኤምኤስ የደንበኞች አገልግሎት ጥራት ሽልማት መቀበሉን ስንገልጽ በላቀ ደስታ ነው! በበርን በሚገኘው በዩፒዩ አለምአቀፍ ቢሮ የተበረከተው ይህ ሽልማት የ#ExpressMail አገልግሎቶችን ከከፍተኛ የደንበኛ እንክብካቤ ጥራት ጋር ለማቅረብ ያለንን ቁርጠኝነት ያገናዘበ ነው።

መልዕክትዎችዎን በጥንቃቄ እና በሙያዊ ብቃት ለመላክ እና ለመቅበል ስላመኑን ደንበኞቻችን ከልብ እያመሰገንን ይህንን የልህቀት ሽልማት እውን እንዲሆን ተግተው ለሚሰሩት ለመላው የኢትዮጵያ ፖስታ ሰራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን እንላለን።

We are thrilled to announce that #Ethiopost has been honored with the EMS Customer Care Award for 2023! This prestigious award, presented at the UPU International Bureau in Berne, recognizes our commitment to delivering exceptional #ExpressMail services with the highest standard of customer care.

A big thank you to our dedicated team and to you, our valued customers, for trusting us to handle your important shipments with care and professionalism. Here’s to continuing our journey of excellence together!

Ethiopia #CustomerServiceExcellence

More updates Ethiopost

News

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ የመታሰቢያ ቴምብሮች በይፉ አስመረቀች።

የኢትዮጵያ ፖስታ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና ታሪካዊ እሴቶቻችንን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። ይህንን ታላቅ ኩነት አስመልክቶ የወጣው ልዩ የመታሰቢያ ቴምብርም ተቋማችን የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ስኬት ለዓለም በማብሰር ረገድ ያለውን ሚና የሚያጎላ ነው።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ስምምነት ተፈራረሙ።

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ኩባንያ “ልባም” የተሰኘውን የዲጂታል የህይወት መድን መተግበሪያ በመላው ሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ መድረክ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ተሸላሚ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU) የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ቀዳሚነቱን ሲያረጋግጥ፣ ከመላው ዓለም ደግሞ 6ኛ ደረጃን በመያዝ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል።

Read More »
News

በኢትዮጵያ ፖስታ እና በአሐዱ ባንክ መካከል በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

የኢትዮጵያ ፖስታ በአገልግሎት ማስፋፋት እና በፋይናንስ ዘርፍ የሚደረጉ ትብብሮችን በማጠናከር ለህብረተሰቡ የቀረበ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለማቅረብ እየሠራ ባለው ሥራ ላይ ይህ የስምምነት ፊርማ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።

Read More »