ቁልፍ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በመላው አፍሪካ የፖስታ እና የአቪዬሽን አገልግሎቶች ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል መድረክ ተዘጋጅቷል። ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ አቶ አቤል አለሙ ጋር በጋራ በመሆን በመላው አህጉር የፖስታ አገልግሎቶችን ለማስጀመር፣ ለማስፋፋት እንዲሁም ለማጠናከር የሚረዱ ስልቶች ላይ በጋራ ለመዳሰስ እድሉን አግኝተናል። ይህ ጥምረት በአህጉር ደረጃ የፖስታ አገልግሎቶችን ውጤታማነት፣ አስተማማኝነት እና የአገልግሎት መሳለጥን የሚያሻሽል ስርዓት ለመፍጠር ያለመ ነው።
In a transformative meeting, Ethiopost engaged with H.E Dr. Sifundo Chief Moyo, Secretary General of PAPU, and Ato. Abel Alemu, MD of Ethiopian Airlines Cargo. This strategic collaboration envisions elevating postal and logistic services across Africa, fostering efficiency, reliability, and interconnectedness.