የኢትዮጵያ ፖስታ በ2016 ዓ.ም “የምትተክል አገር፣የሚያፀና ትውልድ!” በሚል መሪ ሀሣብ እየተከናወነ በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል!
በትናንትናው ዕለት በተካሄደው መርሃግብር ላይ በዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ መሪነት ከድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ አመራር ቡድን ጋር በመሆን ዛፎችን በተመረጡ ቦታዎች በመትከል ለአረንጓዴ አሻራ አስተዋፅዖ አድርጓል። ይህ ተግባር የኢትዮጵያ ፖስታ ለአካባቢ ጥበቃ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያጎላ ብቻ ሳይሆን የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድ ያለውን አስተዋጽኦ እና ጠቀሜታ አጉልቶ የሚያሣይ ነው።
ለቀጣይ ትውልድ አረንጓዴ እና ከአየር ንብረት መዛባት የፀዳ ከባቢን እንፍጠር!
#green_legacy
#Ethiopost
#የምትተከል_አገር_የሚያፀና_ትውልድ!