ኢትዮጵያ ፖስታ በመቄዶኒያ ላሉ ተረጂዎች የሚውል ከ300,000 ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ መገልገያ ቁሳቁሶችን አስረክቧል።በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የሰው ሃብት አስተዳደር ሃላፊ የሆኑት አቶ ተሾመ ቢረዳ እንዲሁም የንብረት አስተዳደር ክፍል ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ይፍቱስራ መኮንን መገልገያ ቁሳቁሶቹን ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር ያስረከቡ ሲሆን የመቄዶኒያ አረጋዉያን የቡራኬ ስነስርዓት አድርገዋል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ፖስታ ከ700,000 ብር በላይ የሚገመት የቢሮ መገልገያ እቃዎች ያስረከበ ሲሆን በቀጣይም የኢትዮጵያ ፖስታ ለመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኅበር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዘበዋል።

News
የኢትዮጵያ ፖስታ በደንበኞች አገልግሎት ጥራት ተሸላሚ ሆነ።
የአለም አቀፉ የፖስታ ህብረት 28ኛው ጠቅላላ ጉባዬ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ባሳየው የላቀ አፈፃፀም የ2024 የፈጣን መልእክት የደንበኞች አገልግሎት ጥራት ሽልማትን ተቀብሏል።











