የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የስራ አመራር ቡድን ከሰራተኞች ጋር በድሬዳዋ፣ በደሴ፣ ሀዋሳ፣ በጅማ እና መቀሌ ከተሞች ለቀናት የቆየ ስብሰባ አድርጓል፡፡ በስብሰባው የድርጅቱን የሶስት አመታት ስትራቴጂ የማጋራት እና የግማሽ አመት የስራ አፈጻጸም ግምገማን መሪ አካል ያደረገ ነበር። ስብሰባው ተቋሙ አሁንም በልህቀት እና በቅልጥፍና ስራውን እንዲቀጥል የሚያበረታታ እንደነበር ተሳታፊዎች ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና መስሪያ ቤት፣ አጠቃላይ ፖስታ ቤት እና የማዕከላዊ ወረዳ ቅርንጫፎች የግማሽ አመታዊ አፈፃፀምን በተመለከተ የተደረገው ስብስባ ላይ በንቃት ተሳትፈዋል።
በድሬዳዋ ከተማ ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር ከተደረገው ውይይት የተወሰዱ ምስሎች ።
በደሴ እና ሀዋሳ ከተማ ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር ከተደረገው ውይይት የተወሰዱ ምስሎች ።
በጅማ እና መቀሌከተማ ከተቋሙ ሰራተኞች ጋር ከተደረገው ውይይት የተወሰዱ ምስሎች ።