የኢትዮጲያ ፖስታ አመራር አባላት የሶስት አመት ስትራቴጂክ እቅዱን ለዋና ዋና ባለድርሻ አካላት ያቀረበ ሲሆን ከነዚህም መካከል የገንዘብ ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ እና የሚመለከታቸው የፓርላማ ንዑስ ኮሚቴ አባላትን ያካትታል። ስብሰባው ተቋሙ ግቡን ለመምታት ያጋጠሙት ተግዳሮቶች ላይ ወሳኝ ውይይት እንዲደረግበት ያደረገ ሲሆን ገንቢ አስተያየቶችን በማሰባሰብ ከባለ ድርሻ አካላት ለድርጅቱ ዓላማ ድጋፍ ለመስጠት ቃል ተገብቷል።
ከውይይቱ በኋላ የኢትዮጲያ ፖስታ አመራር እና ቦርድ የድርጅቱን የስድስት ወራት አፈጻጸም ገምግሟል።