Leadership Team Visit to Teki Paper Bags

የኢትዮጵያ ፖስታ ለአረንጓዴኢትዮጵያ ቁርጠኛ አቋም አለው! የአመራር ቡድናችን በኢትዮጵያ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ለመተካት የሚያስመሰግን ራዕይ ያለውን ተኪ የተሰኘ ድርጅት ጎብኝቷል። Teki ተኪ እስካሁን ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ከ2 ሚሊዮን በላይ የወረቀት ከረጢቶችን በማምረት ለሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞችን እና ሌሎችም ለተገለሉ ወገኖች ትርጉም ያለው መተዳደሪያን እየፈጠረ ነው። የኢትዮጵያ ፖስታ የወደፊት ኢትዮጵያችን ጤናማ እና ለህዝቦቿ አመቺ እንድትሆን ከሚያበረክቱ ተልእኮ ተኮር ድርጅቶች ጋር አጋርነትን ለመፍጠር ተነሳስቷል።

Ethiopost is committed to a greener Ethiopia! Our leadership team paid a visit to Teki Paper Bags, an organization with a commendable vision to replace plastic bags in Ethiopia! Teki has manufactured over 2 million eco-friendly paper bags so far while creating meaningful livelihoods to marginalized groups like women and people with disabilities. Ethiopost is eager to partner with mission-oriented organizations that contribute to a beautiful and healthy future for Ethiopia.

More updates Ethiopost

News

የኢትዮጵያ ፖስታ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲቱት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

ይህ አጋርነት ዘመናዊ የካርታ አሰራርን በኢትዮጵያ ፖስታ ሎጅስቲክስ ማዕቀፍ ውስጥ በማካተት የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን እና ጥራትን ለማሳደግ ያለመ ነው:: ይህንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ፈጣን እና አስተማማኝ የቤት ለቤት እደላ አገልግሎትን በማሳለጥ የደንበኞችን እርካታን ማሻሻል ይቻላል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር የመገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የሰው ሃብት አስተዳደር ሃላፊ የሆኑት አቶ ተሾመ ቢረዳ እንዲሁም የንብረት አስተዳደር ክፍል ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ይፍቱስራ መኮንን መገልገያ ቁሳቁሶቹን ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር ያስረከቡ ሲሆን የመቄዶኒያ አረጋዉያን የቡራኬ ስነስርዓት አድርገዋል።

Read More »
News

የ2024 የእስያ ፊላቴሊክ ኤግዚቢሽን በቻይና።

በሻንጋይ የተካሄደው የ2024 የኤዥያ አለም አቀፍ የቴምብር ኤግዚቢሽን የእስያን ባህል በፊላቴሊ ጥበብ የሚያሳይ ደማቅ በዓል ነበር። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች አስደናቂውን የቴምብር ማሳያ አድንቀዋል፣ እያንዳንዱም የቴምብር ስራዎች ታሪክን፣ ጥበብን እና ወግን ይናገራሉ።

Read More »
News

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮጵያ ፖስታን ጎበኙ።

በክቡር አቶ እውነቱ አለነ የተመራ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት እና የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ፖስታ ሁለንተናዊ ተሃድሶ እንዲሁም አጠቃላይ የስራ ክንውን ላይ ውይይት እና የመስክ ጉብኝት አካሂደዋል።

Read More »