የኢትዮዽያ ፖስታ በስኬት ጉዞ ላይ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጹ።

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቆይታ ለውጡን ተከትሎ በተሰሩ ተከታታይ የሪፎርም ሥራዎች የኢትዮጵያ ፖስታ ከነበሩበት ችግሮች ተላቆ በብዙ የስራ ትጋትና ጥረት በአንዳንድ አገልግሎቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመወዳደር የሚያችል አቅም እንደገነባ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ አክለውም እዚህ ስኬት ላይ የተደረሰው በዋነኝነት የደንበኞች ፍላጎትና የፖስታ አገልግሎት ላይ ጥልቅ ጥናቶችን በማድረግ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ የሀገር ውሰጥ እና ዓለም አቀፍ መዳረሻዎችን በማስፋፋት ፣በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት እንዲሁም የአገልግሎት መስጫዎችን ምቹ የማድረግ ሥራዎችን በመስራት እንደሆነ ተናግረዋል።

በተጨማሪም አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ የኢትዮጵያ ፖስታ በዚህ ሁለንተናዊ ለውጥ በመንግስትም ሆነ በአለም አቀፉ ፖስታ ህብረት ተሸላሚ መሆን እንደቻለ፤ ጥረቶቹንም አጠናክሮ በመቀጠል እና ቀሪ ክፍተቶችን በመሙላት ለተሻለ ስኬት እየተንደረደረ ያለ ልማታዊ የመንግስት ተቋም እንደሆነም ገልፀዋል።

More updates Ethiopost

News

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ላለፉት ተከታታይ አመታት በተሰሩት የሪፎርም ስራዎች ላይ ተመስርቶ ‹‹በጥልቀት እና በስፋት›› በሚል ስትራቴጂክ ፕላን ተቋሙን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራ ያለው ስራ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ሙዚየም 50ኛ ዓመት የወርቅ እዩ ቤልዩ ክብረ በዓል!

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ በክብረ በዓሉ ላይ ለተገኙት እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን እንደተቋም የፖስታ ሙዚየሙ ላይ እየተሠሩ ያሉ የማስፋፊያ ሥራዎች እንዳሉ እና በቅርቡ ይፋ እንደሚደረጉ ገልጸዋል፡፡

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ የሥራ አመራሮች የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም እቅዶች ላይ ከሰራተኞች ጋር ውይይት አደረጉ።

በውይይቱ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ የአቅርቦት እና ፋሲሊቲ ቺፍ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ጋሻው መርሻ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል፤ አያይዘውም በ2017 በጀት ዓመት ለነበረው አፈጻጸም ሁሉም የኢትዮጵያ ፖስታ ሰራተኛ ምስጋና ሊቸረው እንደሚገባ አንስተው በቀጣይም ይኸው የሥራ መነሳሳት እና ተልዕኮዎቻችንን በድል የመወጣት ባሕል ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

Read More »