የታላቁ የእግር ኳስ ሰው መንግሥቱ ወርቁ የመታሰብያ ቴምብር ተሰራለት፡፡

በኃይሌ ግራንድ ሆቴል በተካሄደው የታላቁ የእግር ኳስ ሰው መንግሥቱ ወርቁ የመታሰብያ መርሐ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ያሳተማቸውን ቴምብሮች አስመርቋል፡፡

በዝግጅቱ ላይም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ እና ዲፕሎማት ዶ/ር ተቀዳ ዓለሙ ፣የቀድሞ የትምህርት ሚኒስቴር ዶ/ር ያየህይራድ ቅጣው፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የካፍ ሥራ አስፈጻሚ እና የፊፋ ጸረ-ዘረኝነትና ጸረ-አግላይነት ኮሚቴ አባል አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ የኢ/እ/ፌ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን፣ የመንግሥቱ ወርቁ መታሰብያ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ሰሎሞን በቀለ፣ የመጽሐፉ ጸሐፊ ዶ/ር ሰሎሞን በርኼ፣ የቀድሞ ተጫዋች፣ የኮሚቴ አባላት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የመገናኛ ብዙሀን አካላት በተገኙበት የቴምብር ስራዎች እንዲሁም በስፖርተኛው ላይ ያተኮረ መጽሐፍ ተመርቋል፡፡

በተያያዘም የኢትዮጵያ ፖስታ ከቴምብር ሥራዎች ጀምሮ ለዝግጅቱ ላበረከተው አስተዋጽኦ ዋንጫ የተበረከተለት ሲሆን ከመድረኩም ታላቅ ምስጋና ተችሮታል፡፡

በመጨረሻም የታላቁ የእግር ኳስ ሰው የመንግሥቱ ወርቁን ቤተሰብ በመወከል ንግግር ያደረጉት ፓስተር እሸቴ በቀለ እንደ አጠቃላይ የትኢዮጵያ ፖስታን ጨምሮ ታላላቅ የሀገር ባለውለታዎች እና ባለአደራዎች ይህን መርሐ ግብር በማዘጋጀታቸው በቤተሰብ ስም በማመስገን ስለ መንግሥቱ ወርቁ በስንኝ የታጀበ ምስክርነት አቅርበዋል።

More updates Ethiopost

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን የሙዚየም ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ተበረከተለት።

የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሙዚየም ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ “የተከፋፈለችውን ዓለም የሚያስተሳስሩ ሙዚየሞች” በሚል እጅግ ወቅታዊ መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ በረከት ዘውዴ እና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Read More »
News

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ የመታሰቢያ ቴምብሮች በይፉ አስመረቀች።

የኢትዮጵያ ፖስታ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅና ታሪካዊ እሴቶቻችንን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። ይህንን ታላቅ ኩነት አስመልክቶ የወጣው ልዩ የመታሰቢያ ቴምብርም ተቋማችን የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ስኬት ለዓለም በማብሰር ረገድ ያለውን ሚና የሚያጎላ ነው።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ስምምነት ተፈራረሙ።

የኢትዮጵያ ፖስታ እና የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄኔራል ኢንሹራንስ ኩባንያ “ልባም” የተሰኘውን የዲጂታል የህይወት መድን መተግበሪያ በመላው ሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፍ መድረክ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ተሸላሚ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፉ የፖስታ ህብረት (UPU) የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) የ2025 የጥራት ምዘና ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ቀዳሚነቱን ሲያረጋግጥ፣ ከመላው ዓለም ደግሞ 6ኛ ደረጃን በመያዝ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል።

Read More »