የኢትዮጵያ ፖስታ ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

ይህ ስምምነት 700 በላይ በሚሆኑ የኢትዮጵያ ፖስታ ቅርንጫፎች የሰነዶችን ምዝገባ አገልግሎትን እንዲያካሄድ የሚስችላቸው ነው።
የ2017 ዓ.ም አጠቃላይ አገር አቀፍ የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ገለጻ ለኢትዮጵያ ፖስታ ሰራተኞች ተደረገ።

የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የኘላንና ልማት ሚኒስቴር ቢሮ ያወጣውን ሪፖርት መሰረት በማድረግ ለሰራተኞች አጠቃላይ በተለያዪ ዘርፎች የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ገለጻ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከፍተኛ የስራ አመራሮች የኢትዮጵያ ፖስታን ጎበኙ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከፍተኛ የስራ አመራሮች በዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ እና በምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ኃ/ሚካኤል የተመራ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ልዑክ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና መስሪያ ቤትን የጎበኙ ሲሆን በድርጅቱ የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ላይ ስትራቴጂካዊ ውይይት አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ፖስታ 131ኛ ዓመት የምስረታ በዓል።

በቀድሞ ጊዜ ከነበረው የፖስታ ልውውጥ አሰራር አንስቶ እስከ አሁኑ ዘመናዊ የሎጂስቲክስና የዲጂታል ዘመን ከሁኔታዎችና ወቅታዊ ፍላጐቶች ጋር እራሱን በማስተዋወቅና በማዘመን እንዲሁም የአገልግሎት አድማሱንና ተደራሽነቱን በማስፋት ላለፉት አንድ መቶ ሠላሣ አንድ ዓመታት በትጋትና በአገልጋይነት መንፈስ ተጉዟል።
የኢትዮጵያ ፖስታ – የሰራተኞች ህብረት ቀን በድምቀት ተከበረ።

የኢትዮጵያ ፖስታ የሰራተኞች ህብረት ቀን ላይ ከዋና መስሪያ ቤት እንዲሁም ከሁሉም የዲስትሪክት ቅርንጫፍ የተወጣጡ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች ከጥር 24 እስከ ጥር 25፣ 2017 ዓ.ም ሱሉልታ በሚገኘው በያያ ቪሌጅ በድምቀት አክብሯል።
የኢትዮጵያ ፖስታ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲቱት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

ይህ አጋርነት ዘመናዊ የካርታ አሰራርን በኢትዮጵያ ፖስታ ሎጅስቲክስ ማዕቀፍ ውስጥ በማካተት የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን እና ጥራትን ለማሳደግ ያለመ ነው:: ይህንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ፈጣን እና አስተማማኝ የቤት ለቤት እደላ አገልግሎትን በማሳለጥ የደንበኞችን እርካታን ማሻሻል ይቻላል።
የኢትዮጵያ ፖስታ ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር የመገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የሰው ሃብት አስተዳደር ሃላፊ የሆኑት አቶ ተሾመ ቢረዳ እንዲሁም የንብረት አስተዳደር ክፍል ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ይፍቱስራ መኮንን መገልገያ ቁሳቁሶቹን ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር ያስረከቡ ሲሆን የመቄዶኒያ አረጋዉያን የቡራኬ ስነስርዓት አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ፖስታ ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

በዚህ አብሮ የመስራት ስምምነት ውስጥ የአገልግሎት መስጫ ቦታዎችን ከመጨመር በዘለለ በየወረዳዎቹ ለተደራጁ ስራ ፈላጊ ወጣቶች የስራ ዕድልም የሚፈጥር ነው።
የኢትዮጵያ ፖስታ ከቶፓን ግራቪቲ ኢትዮጵያ ጋር አብሮ የመስራት ስምምነት ተፈራረመ።

ይህ የሥራ ስምምነት ጥራቱን የጠበቀና አስተማማኝ የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ ለነዋሪዎች በተቀላጠፈና በዘመነ መልኩ ለማቅረብ የሚያስችል ነው።
የ2024 የእስያ ፊላቴሊክ ኤግዚቢሽን በቻይና።

በሻንጋይ የተካሄደው የ2024 የኤዥያ አለም አቀፍ የቴምብር ኤግዚቢሽን የእስያን ባህል በፊላቴሊ ጥበብ የሚያሳይ ደማቅ በዓል ነበር። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች አስደናቂውን የቴምብር ማሳያ አድንቀዋል፣ እያንዳንዱም የቴምብር ስራዎች ታሪክን፣ ጥበብን እና ወግን ይናገራሉ።