የኢትዮጵያ ፖስታ የሥራ አመራሮች የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም እቅዶች ላይ ከሰራተኞች ጋር ውይይት አደረጉ።

በውይይቱ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ የአቅርቦት እና ፋሲሊቲ ቺፍ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ጋሻው መርሻ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል፤ አያይዘውም በ2017 በጀት ዓመት ለነበረው አፈጻጸም ሁሉም የኢትዮጵያ ፖስታ ሰራተኛ ምስጋና ሊቸረው እንደሚገባ አንስተው በቀጣይም ይኸው የሥራ መነሳሳት እና ተልዕኮዎቻችንን በድል የመወጣት ባሕል ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ የ2017 በጀት አመት አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 በጀት አመት እቅድ ውይይት አካሄደ።

ለሁለት ቀናት በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም በድርጅቱ የስትራቴጂክ ምሰሶዎች ላይ ተመስርቶ የቀረበ ሪፖርት እና የቀጣይ በጀት አመት እቅዶች በስፋት የተቃኙበት ነበር። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም የተመዘገበበት እንደሆነ የተነሳ ሲሆን እንደተቋም በቀጣይ ትኩረት ሊሰጥባቸው ይገባል ተብለው በዝርዝር የቀረቡ ጉዳዮች ላይም ውይይት ተደርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ ሰራተኞች ሰባተኛውን ዙር ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር አካሄዱ።

የኢትዮጵያ ፖስታ ሰራተኞች ‹‹በመትከል ማንሰራራት›› በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለውን ሰባተኛውን ዙር ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር አካሄዱ።
የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት ውሎች ዝግጅት በኢትዮጵያ ፖስታ

የኢትዮጵያ ፖስታ ከሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት በተሰጠው ውክልና መሰረት የውል ጽሁፎችን በማሰናዳት እናንተን ለማገልገል ከዛሬ ሐምሌ 1 ፣ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተመረጡ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት ጀምራል።
የኢትዮዽያ ፖስታ በስኬት ጉዞ ላይ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጹ።

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቆይታ ለውጡን ተከትሎ በተሰሩ ተከታታይ የሪፎርም ሥራዎች የኢትዮጵያ ፖስታ ከነበሩበት ችግሮች ተላቆ በብዙ የስራ ትጋትና ጥረት በአንዳንድ አገልግሎቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመወዳደር የሚያችል አቅም እንደገነባ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ፖስታ በአዲስ አበባ በተካሄደው የዲጂታል ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ወርክሾፕ ላይ ተሳተፈ።

የኢትዮጵያ ፖስታ ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተካሄደው የዲጂታል ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ወርክሾፕ ላይ ተሳተፈ።
የዓለምአቀፍ የፖስታ ህብረት በፖሰታ አባል አገራት መካከል ለሚደረግ የፖስታ መልዕክቶች ልውውጥ የክፍያ ስርዓት በተመለከተ ለስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ሥልጠና ሰጠ፡፡

የዓለምአቀፍ የፖስታ ህብረት በፖሰታ አባል አገራት መካከል ለሚደረግ የፖስታ መልዕክቶች ልውውጥ /UPU Remuneration System/ የክፍያ ስርዓት በተመለከተ ለስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ሥልጠና ሰጠ፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

የስምምነቱ ዋና አላማ የመንገድ ፈንድ እድሳትን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የአገልግሎት መስጫ ቅርንጫፎች እና በዓመታዊ የተሽከርካሪ ቴክኒክ ደህንነት ምርመራ ተቋማት እንዲኖር ማድረግ ሲሆን ሁሉንም አገልግሎት በአንድ ቦታ መስጠት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮዽያ ፖስታ ከፍተኛ የስራ ሐላፊዎች ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የበላይ አመራሮች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

የኢትዮዽያ ፖስታ ከፍተኛ የስራ ሐላፊዎች ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የበላይ አመራሮች ጋር በቀጣይ በጋራ መስራት በሚቻለባቸው ጉዳዮች ላይ በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ተወካዮች በኢትዮጵያ ፖስታ ጉብኝት እና ውይይት አደረጉ።

በዛሬው ዕለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ተወካዮች በኢትዮጵያ ፖስታ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ጉብኝት እና ውይይት አደረጉ።