የኢትዮጲያ ፖስታ ገንዘብ ነክ የሆኑ እና ያልሆኑ አገልግሎቶችን በመላው ኢትዮጵያ እያሳደገ ይገኛል።

የኢትዮጲያ ፖስታ ከመንግስት፣ ከፋይናንሺያል አገልግሎት ሰጪዎች እና ከሞባይል ኔትወርክ ኦፕሬተሮች ጋር በመተባበር የገንዘብ ነክ የሆኑ እና ያልሆኑ አገልግሎቶችን በመላው ኢትዮጵያ እያሳደገ ይገኛል። አላማችን የእርስዎ ተመራጭ የአገልግሎት መዳረሻ አጋር መሆን ነው። በቅርቡ በኡጋንዳ ከኢትዮጲያ ፖስታ ቡድን ጋር የተደረገ የእውቀት ልውውጥ ጉብኝት አዳዲስ ግንዛቤዎችን ፈጥሯል፣ ለዚህም Amarante Consulting እና Bill and Melinda Gates Foundation ስለ ድጋፋቸው እናመሰግናለን። Posta Uganda Limited፣ Uganda Bankers’  Association፣ Financial Sector Deepening Uganda (FSD Uganda)፣ Agent Banking Company፣ MTN Uganda PostBank Uganda Ltd፣ እና Interswitch Groupን ጨምሮ ለኡጋንዳ አጋሮቻችን የጋራ ራዕይ  ብሎም ስላደረጉልን መልካም እንግዳ ተቀባይነት ከልብ እናመሰግናለን።

More updates Ethiopost

News

የኢትዮጵያ ፖስታ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲቱት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

ይህ አጋርነት ዘመናዊ የካርታ አሰራርን በኢትዮጵያ ፖስታ ሎጅስቲክስ ማዕቀፍ ውስጥ በማካተት የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን እና ጥራትን ለማሳደግ ያለመ ነው:: ይህንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ፈጣን እና አስተማማኝ የቤት ለቤት እደላ አገልግሎትን በማሳለጥ የደንበኞችን እርካታን ማሻሻል ይቻላል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር የመገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የሰው ሃብት አስተዳደር ሃላፊ የሆኑት አቶ ተሾመ ቢረዳ እንዲሁም የንብረት አስተዳደር ክፍል ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ይፍቱስራ መኮንን መገልገያ ቁሳቁሶቹን ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር ያስረከቡ ሲሆን የመቄዶኒያ አረጋዉያን የቡራኬ ስነስርዓት አድርገዋል።

Read More »
News

የ2024 የእስያ ፊላቴሊክ ኤግዚቢሽን በቻይና።

በሻንጋይ የተካሄደው የ2024 የኤዥያ አለም አቀፍ የቴምብር ኤግዚቢሽን የእስያን ባህል በፊላቴሊ ጥበብ የሚያሳይ ደማቅ በዓል ነበር። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች አስደናቂውን የቴምብር ማሳያ አድንቀዋል፣ እያንዳንዱም የቴምብር ስራዎች ታሪክን፣ ጥበብን እና ወግን ይናገራሉ።

Read More »
News

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮጵያ ፖስታን ጎበኙ።

በክቡር አቶ እውነቱ አለነ የተመራ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት እና የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ፖስታ ሁለንተናዊ ተሃድሶ እንዲሁም አጠቃላይ የስራ ክንውን ላይ ውይይት እና የመስክ ጉብኝት አካሂደዋል።

Read More »