News and Updates from Ethiopost
የኢትዮጵያ ፖስታ – የሰራተኞች ህብረት ቀን በድምቀት ተከበረ።
የኢትዮጵያ ፖስታ የሰራተኞች ህብረት ቀን ላይ ከዋና መስሪያ ቤት እንዲሁም ከሁሉም የዲስትሪክት ቅርንጫፍ የተወጣጡ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች ከጥር 24 እስከ ጥር 25፣ 2017 ዓ.ም ሱሉልታ በሚገኘው በያያ ቪሌጅ በድምቀት አክብሯል።

የኢትዮጵያ ፖስታ ኢትዮ-ጆብስ በሚያዘጋጀው አመታዊ የስራ ትርኢት ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ተሳትፏል።
የኢትዮጵያ ፖስታ ኢትዮ-ጆብስ በሚያዘጋጀው አመታዊ የስራ ትርኢት ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ከጥቅምት 27 – 28 ተሳትፏል።

የኢትዮጵያ ፖስታ እና ኦሮሚያ ጤና ቢሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ላይ ያተኮረ ስትራቴጂያዊ ውይይት አደረጉ።
የኢትዮጵያ ፖስታ ከኦሮሚያ ጤና ቢሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመገናኘት በክልሉ የሚገኙ የጤና ናሙና ሎጂስቲክስ፣ የፋይናንሺያል እና የመልዕክት አገልግሎቶችን በቅንጅት መስጠት ላይ ያተኮረ የትብብር ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሂዷል።

በኢትዮጵያ ፖስታ እና በኢግልድ የሸቀጦች ጅምላ ንግድ አስመጪ ድርጅት መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ::
በኢትዮጵያ ፖስታ እና በኢግልድ የሸቀጦች ጅምላ ንግድ አስመጪ ድርጅት መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ::

በኢትዮጵያ ፖስታ እና በኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ ሃውስ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ::
በኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ እና በኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ ሃውስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኤልያብ ጌታቸው የተፈረመው ይህ የአጋርነት ሰነድ የቤት ለቤት መልእክቶችን እና ሌሎች የመልዕክት ልውውጥ አገልግሎቶችን ለደንበኞች ለማድረስ የሚያስችል ነው።

በየኢትዮጵያ ፖስታ እና በኦሮምያ ባንክ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ ::
በየኢትዮጵያ ፖስታ ኮሜርሺያል ቺፍ ኦፊሰር ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ እና በኦሮምያ ባንክ የሪቴል እና ኤስ ኤም ኢ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ጆቴ ቀናቴ የተፈረመው ይህ አጋርነት ከ700 በላይ ቅርንጫፎች ባሉት የኢትዮጵያ ፖስታ የባንክ አገልግሎቶችን በወኪልነት እንዲሰራ የሚያስችል ነው።

የዓለም ባንክ እና የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በየኢትዮጵያ ፖስታ ጉብኝት አካሄዱ።
የአለም ባንክ እና የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያ ካርዶችን በማተም እና በማሰራጨት ላይ ያለውን የሥራ ሂደት እንዲሁም የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥን በየኢትዮጵያ ፖስታ በመገኘት ተመልክተዋል።