News and Updates from Ethiopost
የኢትዮጵያ ፖስታ የ ሳጥን አልባ መልዕክት አገልግሎት እንዲሁም የፖስታ ገበያ መተግበሪያዎችን በይፋ አስመረቀ፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ ያበለጸጋቸውን የ ሳጥን አልባ መልዕክት አገልግሎት እንዲሁም የፖስታ ገበያ መተግበሪያዎችን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የኢትዮጵያ ፖስታ የቦርድ አባላት፣ የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ባለቤቶች በተገኙበት በስካይ ላይት ሆቴል በይፋ አስመርቋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ተወካዮች በኢትዮጵያ ፖስታ ጉብኝት እና ውይይት አደረጉ።
በዛሬው ዕለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ተወካዮች በኢትዮጵያ ፖስታ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ጉብኝት እና ውይይት አደረጉ።

የኢትዮጵያ ፖስታ ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።
ይህ ስምምነት 700 በላይ በሚሆኑ የኢትዮጵያ ፖስታ ቅርንጫፎች የሰነዶችን ምዝገባ አገልግሎትን እንዲያካሄድ የሚስችላቸው ነው።

የ2017 ዓ.ም አጠቃላይ አገር አቀፍ የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ገለጻ ለኢትዮጵያ ፖስታ ሰራተኞች ተደረገ።
የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የኘላንና ልማት ሚኒስቴር ቢሮ ያወጣውን ሪፖርት መሰረት በማድረግ ለሰራተኞች አጠቃላይ በተለያዪ ዘርፎች የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ገለጻ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከፍተኛ የስራ አመራሮች የኢትዮጵያ ፖስታን ጎበኙ።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከፍተኛ የስራ አመራሮች በዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ እና በምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ኃ/ሚካኤል የተመራ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ልዑክ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና መስሪያ ቤትን የጎበኙ ሲሆን በድርጅቱ የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ላይ ስትራቴጂካዊ ውይይት አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ፖስታ 131ኛ ዓመት የምስረታ በዓል።
በቀድሞ ጊዜ ከነበረው የፖስታ ልውውጥ አሰራር አንስቶ እስከ አሁኑ ዘመናዊ የሎጂስቲክስና የዲጂታል ዘመን ከሁኔታዎችና ወቅታዊ ፍላጐቶች ጋር እራሱን በማስተዋወቅና በማዘመን እንዲሁም የአገልግሎት አድማሱንና ተደራሽነቱን በማስፋት ላለፉት አንድ መቶ ሠላሣ አንድ ዓመታት በትጋትና በአገልጋይነት መንፈስ ተጉዟል።

የኢትዮጵያ ፖስታ – የሰራተኞች ህብረት ቀን በድምቀት ተከበረ።
የኢትዮጵያ ፖስታ የሰራተኞች ህብረት ቀን ላይ ከዋና መስሪያ ቤት እንዲሁም ከሁሉም የዲስትሪክት ቅርንጫፍ የተወጣጡ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች ከጥር 24 እስከ ጥር 25፣ 2017 ዓ.ም ሱሉልታ በሚገኘው በያያ ቪሌጅ በድምቀት አክብሯል።
