የኢትዮጵያ ፖስታ የሰራተኞች ቀን በደመቀ ሁኔታ ተከበረ።

የኢትዮጵያ ፖስታ የሰራተኞችን ትጋት፣ ቁርጠኝነትና ስኬት ለማክበር እና ለማጠናከር ያዘጋጀው ዓመታዊ የሰራተኞች ቀን ዝግጅት በ ጥር 16 እና 17/2018 ዓ.ም በተለያዩ አበረታችና አዝናኝ መርሐ ግብሮች በደማቅ መንፈስ ተከናውኗል።

በመክፈቻው ስነ-ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ተገኝተው፣ ለላቀ አፈጻጸም ያሳዩ ሰራተኞች እንዲሁም በፖስታ ገበያ (Posta Gebeya) እና ቨርቹዋል ፖስታ ሳጥን አገልግሎቶች ዝግጅት እና ትግበራ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አመራሮችና ሰራተኞች የምስጋና እውቅና እና ምስክር ወረቀት ሰጥተዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው በንግግራቸው በቀጣይ ተቋማዊ ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ሰራተኛ በከፍተኛ መነሳሳትና ቁርጠኝነት መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል። በዝግጅቱ ላይ ከሁሉም ዲስትሪክቶች በተወጣጡ ሰራተኞች መካከል የአንድነትና የቡድን መንፈስን የታየባቸው የእግር ኳስ ግጥሚያዎች ተካሂደዋል፡፡

በቀጣዩ ቀን በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው በከፍተኛ አመራሮች እና በዲስትሪክት ዳይሬክተሮች መካከል የተካሄደው እና በአዝናኝነት የተሞላው የእግር ኳስ ግጥሚያ በመጨረሻ በከፍተኛ አመራሮች አሸናፊነት ተጠናቋል።

ከዚህ በተጨማሪ በሁለቱም ጾታ የዕለቱን ድባብ ከፍ ያደረጉ እና እድምተኞችን ያዝናኑ የእግር ኳስ ግጥሚያ፣ የገመድ ጉተታ፣ የማዳበሪያ ዝላይ እና እንቁላል በአፍ ይዞ መሮጥ ውድድሮች ተካሂደዋል:: በመዝጊያው እለት ለዘመናት ተቋሙን በታማኝነት ያገለገሉ እና በጡረታ ለሚለዩ አንጋፋ ሰራተኞችም የክብር አሸኛኘት ተደርጓል።

More updates Ethiopost

News

በኢትዮጵያ ፖስታ እና በአሐዱ ባንክ መካከል በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

የኢትዮጵያ ፖስታ በአገልግሎት ማስፋፋት እና በፋይናንስ ዘርፍ የሚደረጉ ትብብሮችን በማጠናከር ለህብረተሰቡ የቀረበ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለማቅረብ እየሠራ ባለው ሥራ ላይ ይህ የስምምነት ፊርማ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ከM-PESA ኢትዮጵያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ።

የኢትዮጵያ ፖስታ ከ M-PESA ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ባሉት ከ 1000 በላይ ቅርንጫፎች አማካይነት የM-PESA አገልግሎትን እንደ ዋና ወኪል በመሆን ለደንበኞቹ ማቅረብ የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ 132ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እና የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበረ፡፡

በዕለቱ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ለመላው የኢትዮጵያ ፖስታ ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ ፖስታ 132ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እንዲሁም ለዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

Read More »
News

የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጉብኝት አካሄዱ፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ጉብኝቱ ላይ ባዩዋቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች እና የሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እየተሰሩ ባሉት ሥራዎች ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

Read More »