በኢትዮጵያ ፖስታ እና በኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ ሃውስ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ::

በኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ እና በኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ ሃውስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኤልያብ ጌታቸው የተፈረመው ይህ የአጋርነት ሰነድ የቤት ለቤት መልእክቶችን እና ሌሎች የመልዕክት ልውውጥ አገልግሎቶችን ለደንበኞች ለማድረስ የሚያስችል ነው።

በየኢትዮጵያ ፖስታ እና በኦሮምያ ባንክ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ ::

በየኢትዮጵያ ፖስታ ኮሜርሺያል ቺፍ ኦፊሰር ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ እና በኦሮምያ ባንክ የሪቴል እና ኤስ ኤም ኢ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ጆቴ ቀናቴ የተፈረመው ይህ አጋርነት ከ700 በላይ ቅርንጫፎች ባሉት የኢትዮጵያ ፖስታ የባንክ አገልግሎቶችን በወኪልነት እንዲሰራ የሚያስችል ነው።

የዓለም ባንክ እና የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በየኢትዮጵያ ፖስታ ጉብኝት አካሄዱ።

የአለም ባንክ እና የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያ ካርዶችን በማተም እና በማሰራጨት ላይ ያለውን የሥራ ሂደት እንዲሁም የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥን በየኢትዮጵያ ፖስታ በመገኘት ተመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፖስታ የስራ ላይ ልምምድ ሲያደርጉ ለነበሩ አዲስ ተመራቂ ተማሪዎች በሰርተፊኬት እውቅና ሰቷል።

በፋይናንስ፣ በሰው ሃይል አስተዳደር፣ በደንበኛ አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች የስራ ክፍሎች ውስጥ ተመድበው ሲሠሩ የነበሩ ተማሪዎችን ለ 2 ወራት በቆየ የስራ ላይ ልምምድ በማሰማራት ስለ ስራው በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው አድርጓል።

የኢትዮጵያ ፖስታ የ2017 ዓ.ም የዓዲስ ዓመት ዋዜማን በዋናው መስሪያ በደመቀ ሁኔታ አክብሯል።

ይህ ማዕድ በመጋራት፣ በአብሮነት፣ በሚፍለቀለቁ ሳቆች እና በውድ ጊዜዎች የተሞላው የአዲስ አመት  ዋዜማ አከባበር መጪው ዘመን በስኬት የተሞላ ይሆን ዘንድ በህብረት እና በትጋት የመስራት አስፈላጊነትንም የሚያሳይ ነበር።