የኢትዮጵያ ፖስታ ነባር የቦርድ አባላት የሽኝት እና ለአዲሱ ቦርድ አባላት የአቀባበል ስነስርአት ተካሄደ።

በሽኝት ሥነሥርዓቱ ላይ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ የተቋሙ የስትራቴጂ እቅድ ግቡን እንዲመታ የቦርድ አባላቱ ያበረከቱትን ጉልህ አስተዋፅኦ በማንሳት በኢትዮጵያ ፖስታ ውስጥ ትልቁን ታሪክ እንደፃፉ እና ትልቅ ምስጋና እና ክብር እንደሚገባቸው ገልፀዋል።
22ኛው የዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በኢትዮጵያ ፖስታ ተከብሯል።

“ትውልድን በስነምግባር ተቋምን በአሰራር” በሚል መሪ ቃል 22ኛው የዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ አመራሮች እና ሠራተኞች በተገኙበት ተከብሮ ውሏል።
የታላቁ የእግር ኳስ ሰው መንግሥቱ ወርቁ የመታሰብያ ቴምብር ተሰራለት፡፡

በኃይሌ ግራንድ ሆቴል በተካሄደው የታላቁ የእግር ኳስ ሰው መንግሥቱ ወርቁ የመታሰብያ መርሐ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ያሳተማቸውን ቴምብሮች አስመርቋል፡፡
በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የተመራው የብሔራዊ ኢ-ኮሜርስ ኮሚቴ ልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ ፖስታ ጉብኝት እና ውይይት አደረገ።

በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ይድነቃቸው ወልደተንሳይ የተመራው የብሔራዊ ኢ-ኮሜርስ ኮሚቴ ልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ ፖስታ ጉብኝት እና ውይይት አደረገ፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መልእክት።

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምርቃትን አስመልክቶ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። በመልእክታቸው ላይ የግድቡ መጠናቀቅ እንደ ሃገር የሚፈጥረውን ትልቅ አቅም ገልጸው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ባበረከተው አስተዋጽኦ ሊኮራ እንደሚገባ ገልጸዋል።ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ በማለት መጪው አዲስ ዓመት የሰላም፣ የደስታ እንዲሁም የብልጽግና እንዲሆን […]
የኢትዮጵያ ፖስታ በደንበኞች አገልግሎት ጥራት ተሸላሚ ሆነ።

የአለም አቀፉ የፖስታ ህብረት 28ኛው ጠቅላላ ጉባዬ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ባሳየው የላቀ አፈፃፀም የ2024 የፈጣን መልእክት የደንበኞች አገልግሎት ጥራት ሽልማትን ተቀብሏል።
በኢትዮጵያ ፖስታ እና በቲና ማርት መካከል የጋራ መግባቢያ ሠነድ ተፈረመ።

የኢትዮጵያ ፖስታ በኦን ላይን የግብይት ስርዓቱ ላይ በአጭር ግዜ ውስጥ ትልቅ ልዩነትን እየፈጠረ ከሚገኘው ቲና ማርት ጋር አብሮ የመስራት ስምምነት ተፈራርሟል።
የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ላለፉት ተከታታይ አመታት በተሰሩት የሪፎርም ስራዎች ላይ ተመስርቶ ‹‹በጥልቀት እና በስፋት›› በሚል ስትራቴጂክ ፕላን ተቋሙን ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራ ያለው ስራ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ ሙዚየም 50ኛ ዓመት የወርቅ እዩ ቤልዩ ክብረ በዓል!

የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ በክብረ በዓሉ ላይ ለተገኙት እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን እንደተቋም የፖስታ ሙዚየሙ ላይ እየተሠሩ ያሉ የማስፋፊያ ሥራዎች እንዳሉ እና በቅርቡ ይፋ እንደሚደረጉ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጉብኝት፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንጦጦ በሚገኘው የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ እና የምርምር ማዕከልን ጎበኙ፡፡