News and Updates from Ethiopost
የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፉ የፖስታ ሕብረት የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) ጥራት ምዘና ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነ።
የኢትዮጵያ ፖስታ በዓለም አቀፉ የፖስታ ሕብረት የፈጣን መልዕክት አገልግሎት (EMS) ጥራት ምዘና ከአፍሪካ ቀዳሚ በመሆን ከመላው ዓለም ደግሞ 6ኛ ደረጃ ላይ መመደቡ በይፋ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ፖስታ እና በአሐዱ ባንክ መካከል በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።
የኢትዮጵያ ፖስታ በአገልግሎት ማስፋፋት እና በፋይናንስ ዘርፍ የሚደረጉ ትብብሮችን በማጠናከር ለህብረተሰቡ የቀረበ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለማቅረብ እየሠራ ባለው ሥራ ላይ ይህ የስምምነት ፊርማ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ፖስታ ከM-PESA ኢትዮጵያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ።
የኢትዮጵያ ፖስታ ከ M-PESA ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ባሉት ከ 1000 በላይ ቅርንጫፎች አማካይነት የM-PESA አገልግሎትን እንደ ዋና ወኪል በመሆን ለደንበኞቹ ማቅረብ የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።

የኢትዮጵያ ፖስታ 132ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እና የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበረ፡፡
በዕለቱ የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ለመላው የኢትዮጵያ ፖስታ ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ ፖስታ 132ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እንዲሁም ለዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን እንኳን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጉብኝት አካሄዱ፡፡
የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ጉብኝቱ ላይ ባዩዋቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች እና የሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እየተሰሩ ባሉት ሥራዎች ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ የአየር ኃይላችንን 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ያዘጋጃቸውን አራት አይነት ታሪካዊ ቴምብሮች በይፋ አስመርቋል።
ዛሬ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የተመሰረተበትን 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አክብሯል። የኢትዮጵያ ፖስታ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ ለመዘከር ያሳተማቸውን አራት አይነት ልዩ የመታሰቢያ ቴምብሮች በይፋ አስመርቋል።

የኢትዮጵያ ፖስታ የሰራተኞች ቀን በደመቀ ሁኔታ ተከበረ።
የኢትዮጵያ ፖስታ የሰራተኞችን ትጋት፣ ቁርጠኝነትና ስኬት ለማክበር እና ለማጠናከር ያዘጋጀው ዓመታዊ የሰራተኞች ቀን ዝግጅት በ ጥር 16 እና 17/2018 ዓ.ም በተለያዩ አበረታችና አዝናኝ መርሐ ግብሮች
